2011-06-17 14:44:39

ሊትዋኒያ፦ የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት “አስፍሆተ ወንጌል እና የመገናኛ ብዙኃን”


አዲስ አስፍሆተ ወንጌል በኤውሮጳ በሚል ርእሰ ጉዳይ የተመራ የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶችን የሚያቅፈው የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በዋና ጸሓፊዎች ምክር ቤት የተመራ ስብሰባው እ.ኤ.አ. እስከ ሰኔ 19 ቀን 2011 ዓ.ም. የሚቀጥለው ስብሰባው ከሰኔ 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በሊታዋንያ ርእሰ ከተማ ቪልኒውስ ከተማ እያካሄደ መሆኑ ሲገለጥ፣ ተመሳሳይ ርእሰ RealAudioMP3 ጉዳይ በማስከተል እ.ኤ.አ. እስከ ስኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ኅብረት የመላ ኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳስት ምክር ቤቶች የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪዎች አማካኝነት የሚያካሂደው ስብሰባ ነገ ሰኔ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚጀመር ዜኒት የዜና አገልግሎት ከኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት የተሰራጨ ዜና በማስደግፍ አስታወቀ።

የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ዋና ጸሓፊዎች ትላትና በቪልኒዩስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አውድይስ ዩዛክ ባኪስ አቀባበል ተደረጎላቸው በኤውሮጳ የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ሂደት እና ከባህል ጋር ያለው ግኑኝነት እንዲሁም በቃል እና በሕይወት በሚኖረው እምነት የተካነ በሚሉት አበይት ነጥቦች ላይ በማተኮር ሰፊ ውይይት እያካሄደ መሆኑ ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በመቀጠልም ስብሰባው መንፈሳዊ ሕይወት እና የቤተ ክርስትያን ቤተ ሰብ አባል በተሰየመ ርእስ ተመርቶ በመካሄድ እ.ኤ.አ. ሰኔ 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ከተጠናቀቀ በኋላ ቅዳሜ የመላ ኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪዎች ምክር ቤት ስብሰባ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ማእከል በማድረግ ከተለያዩ የካቶሊክ የመገናኛ ብዙኃን የተወጣጡ የዜና ማኅተም ተጠሪዎች ልኡካን እንደሚሳተፉም የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ያሰራጨው መግለጫ የጠቀሰ ዜኒት የዜና አገልግሎት በማስታወቅ፣ በዚህ ስብሰባ የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፅዕ አቡነ ሳልቫቶረ ፊሲከላ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር የተጀመረም ሲሆን፣ ከዝግ ስብሰባው ፍጻሜ ባኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥም ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.