2011-06-15 15:32:08

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ ስሜተ ጵጵስና


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በታላቅዋ ብሪጣኒያ ለሚኖሩት ለዩክራይን ዜጎች የቢዛንታይን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምእመና ሐዋርያዊ ኤክሳርቆ ማለትም የኤጳርቅና ጳጳስ መሾማቸው የቅድስት መንበር የዜና ኅትመት መግለጫ አስታወቀ።

በሎንደን የቢዛንታይን ሥርዓት ለምክተከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሐዋርያዊ RealAudioMP3 አስተዳዳሪ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙት የነበሩት 57 ዓመት ዕድሜ ያላቸው በተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ከኡክራይ ስደተኛ ቤተሰብ የተወልዱ እዚህ በሮማ በጳጳሳዊ ኡርባኒያኑም መንበረ ጥበብ የመጽሐፍ ቅዱስ ቲዮሎጊያ እና እንዲሁም በጳጳሳዊ የምሥራቅ አቢያተ ክርስያን መንበረ ጥበብ እ.ኤ.አ. በ 2001 ዓ.ም. የሊጡርጊያ ቲዮሎጊያ ሊቅነት ያስመሰከሩ በሮማ የቅድስት ሶፊያ ተቛም ኅየንተ በመሆን እንዳገለገሉም ሲገለጥ፣ ይኸው በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ መሠረት አባ ህሊብ (ቦርይስ ስቪኣቶስላቭ) ሎንቻይና የቤተ ክርስትያኒቱ ጳጳስ እንዲሆኑ መሰየማቸው የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ብፁዕ አቡነ ህሊብ ሎንችይና እ.ኤ.አ. በ 2002 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በሊቪ የቢዛንታይን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ረዳት ጳጳስ እንዲሆኑ መሰየማቸው የቅስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል መግለጫ በመስታወስ፣ በኢጣሊያ የኡክራይን የግሪክ ሥርዓት ለምትከትለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምእመናን ሐዋርያዊ ጎብኝ ብፁዕ ጳጳስ ቀጥለውም በስፐይን እና በአየርላንድ በተመሳሳይ ተልእኮ ካገለገሉ በኋላ እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. በታላቅዋ ብሪጣኒያ ለሚኖሩት ለዩክራይን ዜጎች የቢዛንታይን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምእመና ሐዋርያዊ አስተዳዳሪ ሆነው በማገልግል ላይ እያሉ ይኸው ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለሐዋርያዊ ኤክሳርቆስ ማለት ለኤጳርቅና ጳጳስ ተልእኮ ከፍ በማድረግ ጳጳስ እንዲሆኑ እንደሰየሙዋቸው የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ያሰራጨው ዜና ያመለክታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በቤኒን የናቲቲንጉ ሊቀ ጳጳስ በመሆን በማገልግለ ላይ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ፓስካል ኒኩዌ የፓራኩ ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ እንደሰየሙዋቸው የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.