2011-06-15 15:41:59

ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የሁሉም አባት


የካሚሊያን ገዳማውያን ማኅበር በየወሩ የሚታተመው ካሚሊያኒ የተሰየመው መጽሔት አስተዳዳሪ ጋዜጠኛ ረንዞ አጋሶ የዘመኑ የተለያዩ ታላላቅ እና የአበይት ኣካላት የሕወት ታሪክ ደራሲ በቅርቡ ውድ ካሮል በሚል ርእስ ሥር RealAudioMP3 የደረሱት ለር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የክፍት ደብዳቤ ሥልት የተከተለ መጽሐፍ በኤፋታ ማተሚያ ቤት በኵል ታትሞ ለንባብ መብቃቱ ተገለጠ።

ደራሲው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የመጽሐፉ ርእስ እንደሚያመለክተው በውስጤ ሁሌ ለር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የሚሰማኝን ቅርበት ወዳጅነት የሚገልጥ ከመሆኑም ባሻገር፣ ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ለማንም እንግዳ ሳይሆኑ፣ ቅርብ እና ሩቅ ለሚኖሩ ባጠቅላይ ለሁሉም ቅርብ ቤተኛ መሆናቸው በሕይወት ዘመን እያሉ የኖሩት ባህርያቸው የሚያጎላ መጽሐፍ ነው። ይኽ ለሁሉም ቅርብ የመሆናቸው ቤተኛው ባህርያቸው ቤተ ክርስትያን በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ አማካኝነት በይፋ ብፅዕና በማወጅ እዳስተጋባችውም አስታውሰው፣ ካሮል ውይትይላ በእግዚአብሔ ፍቅር የተሞሉ በእግዚአብሔር ፍቅር ክፍት ለመሆን ያበቃቸው ጸጋ ከእዚአብሔር የታደሉት ከመሆኑም ባሻገር ነጻ ለእግዚአብሔር ሥልጣን እና በላይነት እና ኃይል የተገዙ በሁሉም ሥፍራ የእግዚአብሔር ኅላዌ ያዳመጡ ሁለ መናቸው ለዚህ ኅልውና እንዲያዘነብል በማድረግ እግዚአብሔርን የመሰከሩ በተለይ ደግሞ በሥቃይ ላይ እያሉ የቅዱስ ጴጥሮስ ተክታይ መሆናቸው ሳይዘነጉ እና ሳያቋርጡ እግዚአብሔር ለሰጣቸው ኃላፊነት ታማኝ በመሆን ፍቅሩን የመሰከሩ መሆናቸው የሚተነትን መጽሐፍ ነው በማለት የሰጡት ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.