2011-06-13 14:39:49

የቅድስት መንበር የሕገ ዓንቀጽ ጉዳይ የሚከታተል ጳጳስዊ ምክር ቤት ውሳኔ


ያልተፈቀደ እና ያልተገባ ቅብአተ ጵጵስና ጉዳይ በተመለከተ የቅድስት መንበር የሕገ ዓንቀጽ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ውሳኔ ማስተላለፉ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ሲቻል፣ የአዲሱ ሕገ ውሳኔ ዝርዝር በዚህ የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ታቶሞ ይፋ መደረጉ ሲታወቅ፣ በአዲሱ ሕግ መግቢያ ከባለፉት የመጨረሻ ዓሥር ዓመታት RealAudioMP3 ወዲህ ካለ ቅድስት መንበር ውሳኔ በተለያዩ አገሮች የተፈጸሙት ቅብአተ ጵጵስና እያስክተለው ያለው ችግር በመተንተን ይኽ አለ ቅድስት መንበር ውሳኔ የሚፈጸመው ቅብአተ ጵጵስና ከቅዱስ ጴጥሮት ተከታይ ጋር ያለው ውህደት በማፍረስ እና የቤተ ክርስትያን ሥርዓት በከፍተኛ ደረጃ የሚጥስ መሆኑ በማብራራት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ፣ አለ ቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ውሳኔ በእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ቅብዓተ ጵጵስና አይሰጥም በማለት በሥልጣናዊ ትምህርት መሰረት የዘረዘረውም ሲሆን ስለዚህ ቅድስት መንበር ካለ ሐዋርያዊ መንበር ፈቃድ እና ውሳኔ የሚፈጸመ ቅብአተ ጵጵስና ያልተገባ መሆኑ በማብራራት፣ በሕገ ቀኖና ዓንቀጽ 1382 ያለው ሕግ መሠረት በማድረግ በተሰጠው ማብራሪያ ይኽ እጅግ አንገብጋቢ እና አሳሳቢ የሆነው ጉዳይ በቤተ ክርስትያን ውስጥ እንዳይፈጸም ካለ መታከት ትኩረት በመስጠት ከወዲሁ የሚቻለውን ሁሉ ከማድረግ አልተቆጠበችም፣ ሆኖም ግን በቅድምያ እንዳይከሰት ከምታደርገው ጥረት ባሻገር በሕግ ውሳኔ ሊሰጥበት የተገባ በመሆኑ ምክንያት የተሰጠው የውሳኔ አንቀጽ መሆኑ የሕገ ዓንቀጽ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያስተላለፈው ውሳኔ በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የቅድስት መንበር የዜና ኅትመት ጉዳይ ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አብራርተዋል።

ስለዚህ አለ ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ እና ፈቃድ የሚፈጸመው ቅብአተ ጵጵስና የቤተ ክርስትያን ውህደት የሚነካ አደገኛ ውሳኔ በመሆኑ፣ ስለዚህ ከዚህ አኳያ አንጻር ሲታይ ያለው ክብደት እና ሊያስከትለው የሚችለው እንቅፋት እግምት ውስጥ የሚያስገባ ሲሆን፣ አለ ሓዋርያዊ መንበር ውሳኔ የሚፈጸመው ቅብአተ ጵጵስና የቅብአቱ ሥነ ሥርዓት ፈጻሚ እና ንፍቀ ሰራኢ ላይ በጠቅላላ በሥነ ሥርዓቱ በሚሳተፍ ሁሉ ላይ በሕገ ቀኖና አንቀጽ 1382 የሠፈረው ውሳኔ እንዴት እግብር ላይ መዋል እንዳለበት የሚያብራራ ውሳኔ መሆኑ አባ ሎምባርዲ አስታውቀዋል።

በእንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን ውስጥ አለ ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ ቅብአተ ጵጵስና እንዳይፈጸም ከተፈጸመ ደግሞ ጉዳዩ ተገቢ ውሳኔ እንዲሰጥበት የሚያሳስብ ቢሆንም ቅሉ፣ ተጠያቂ ከሆኑት ጋር ግኑኝነት በማድረግ የተፈጸመው ቅብአተ ጵጵስና የተግባ እንዳልሆነ ቅድስት መንበር ለማዝገንዘብ ትጥራለች፣ በመጨረሻ ምንም’ኳ የእርቅ በር ሁሌ ክፍት በማድረግ ጉዳዩን የምትከታተል ብትሆንም ሥርዓት የማያከብረው ለመመለስ እምቢ የሚል ከሆነ ለማውገዝ የምትገደድ መሆኗ የሚያብራራ ውሳኔ ነው በማለት የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.