2011-06-13 14:38:25

የቅድስት መንበር ርዕሰ ዓንቀጽ፦ የሶሪያው ወታዊው ጉዳይ


በሶሪያ በመንግሥት ወታደሮች እና በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል የተቀጣጠለው ግጭት ከቀን ወደ ቀን አሳሳቢነቱ እጅግ ከፍ እያለ መሆኑ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባለፈው ሰኞ በቅድስት መንበር የሶሪያ ልኡከ መንግሥት እንዲሆኑ ከመንግሥታቸው የተላኩት ሁሳን ኤዲን ዓላን ያቀረቡት የሹመት ደብዳቤ ተረክበው ባሰሙት ንግግር ባሉትን ሃሳብ ላይ ያተኮረ በሳምት RealAudioMP3 መገባደጃ የቅድስት መንበር የዜና ኅትመት ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በማቅረብ፣ በሶሪያ ያለው ውጥረት እልባት ያጣ እንደሚመስል እና ይኽ ደግሞ በጠቅላላ በመካከለኛው ምሥራቅ በአንዳንድ አረብ አገሮች የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ጋር የሚመሳሰል ጉዳይ መሆኑ ገልጠው፣ የሶሪያ ተወላጅ የእየሱሳውያን ማኅበር ካህናት በቅርቡ በሶሪያ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ኅብረአዊነት ላይ የጸናው የአንድነት ባህል ላይ በማተኮር የወቅቱ ሁኔታ ማእከል በማድረግ ባስተላለፉት ሰነድ ኅብረአዊነት ላይ የጸናው አንድነት የታቀበባት አገር ሆና እያለች፣ ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት የተቀሰቀሰው ማህበራዊ ፖለቲካዊ አመጽ ብዙሃኑ የአገሪቱ ዜጋ ያሳተፈ ነው ቢባልም፣ ተቀስቅሶ ያለው ውጥረት ተገን በማድረግ የአገሪቱ ኅብረአዊነት ሰላም ለማናጋት ሃይማኖታዊ ግጭት በመቀስቀስ የሶርያው ኅብረተሰብ ለመከፋፈል ለሚሻ ንቅናቄ በር የከፈተ እንደሚመስል በማብራራት ስለዚህ የተከሰተው ውጥረት ሃይማኖታዊ ማኅበራዊ ግጭት መንሰኤ ሆኖ አገሪቱ ለከፋ አደጋ እንዳያጋልጣት ውይይት እንዲቀድም በማሳሰብ፣ የሶሪያ አገራዊ አንድነት ለአገሪቱ ማኅበረ ክርስትያን ዋስትና ነው። ስለዚህ ክርስትያኖች የተከስተው አመጽ ለማስወገድ የውይይት ድልድይ ሆነው እንዲገኙ የሶሪያ ዜጎች የእየሱሳውያን ማኅበር አባላት ባስተላለፉት መልእክት በመግለጥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሶሪያ ልኡከ መንግሥት በመቀበል ባሰሙት መልእክት የጋራ ውይይት እና የማንኛውም ሰው ሰብአዊ ክብር ጥበቃ ወሳኝ መሆኑ የሰው ልጅ የማኅበራዊ እና የግል ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ ማእከል ያደረገ እውነት ላይ የጸና እርቅ እና ሰላም የሚያነቃቃ እውነተኛ ኅዳሴ ወሳኝ መሆኑ ማብራራታቸው በመጥቀስ፣ በዚሁ ዘርፍ የክርስትያኖች ተሳትፎ ምን መሆን እንዳለበት ቅዱስነታቸው በመተንተን የሶሪያው ማኅበረ ክርስትያን ከምስልምናው ሃይማኖት ጋር በመወያየት ለጋራ ጥቅም መረጋገጥ ይተጉ ዘንድ አደራ እንዳሉ በርእሰ አንቀጹ ተመልክቶ ይገኛል።

በአንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የሚታየው ሕዝቦችን ለመበታተን ብሎም ለመፈናቀል አደጋ የሚያጋልጠው እየተዛመተ በመሄድ ላይ ያለው መቋጫ ያጣው ግጭት ለማስወገድ ሁሉም ለእርቅ እና ለሰላም ይለወጥ ዘንድ ቅዱስ አባታችን ያቅረቡት ጥሪ በማስፈር አባ ሎምባርዲ ርእሰ ዓንቀጹን ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.