2011-06-10 16:00:17

ብፁዕ አቡነ ቶማሲ፦ ለወጣት ትውልድ የሥራ ዕድል የማይፈጥር የኤኮኖሚ እድገት መቃወም


ጀነቭ በሚገኘው ለተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ አስከባሪ ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ቶማሲ በጀነቭ በተካሄደው መቶኛው ዓለም አቀፍ የሥራ እና ሠራተኛ ጉዳይ የሚከታተለው አለም ዓቀፍ ድርጅት ባካሄደው ጉባኤ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ የበለጸጉ አገሮች ከዚህ በፊት ታይቶ እና ተሰምቶ ከማይታወቀው ተከስቶ RealAudioMP3 ከነበረው የኤኮኖሚ እና የቁጠባ ቀውስ ቀስ በቀስ እየተላቀቁ ቢሆንም ቅሉ ሆኖም ግን ግዜው ያለፈበት የሚከተሉት እድገት የሚያስጨብጥ እና እድገት የሚያነቃቃው የኤኮኖሚው ቀመራቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከሰተ ባለው የአለማዊነት የትሥሥሩ ሂደት አስተማማኝ አለ መሆኑ እየተረጋገጠ ነው። ይኽ ደግሞ መንግሥታት በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ አገሮች የሚገኙት በብዙ ሚሊዮን የሚገመተው ሥራ አጥ እና ሥራ ፈላጊው ወጣት የኅብረተሰብ ክፍል ሥራ የማግኘት እድሉ ተገቢ መልስ በመስጠት ለማርካት እንዳይችሉ እያደርጋቸው ነው። ምንም’ኳ በተከሰው የኤኮኖሚው ቀውስ አናሳው የኤክኖሚው አውታር መጠነኛ መሻሻል እያሳየ የንግዱ አለም ኤኮኖሚ ሻል ቢልም የሥራው ንግድ ገና ጎታታ እና የሥራ እድል የመፍጠር አዝማሚያው እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መጥተዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ መጠነኛ የኤክኖሚ እድገት እየታየ ቢሆንም ቅሉ የሥራ ዕድል የማርካት ብቃት የሌለው እየሆነ ነው የሚታየው ካሉ በኋላ፣ የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ቶማሲ አክለው ለሥራ አጥነት ችግር ተገቢ ምላሽ የማይሰጥ እየተከሰተ ያለው የኤክኖሚ እድገት እና ልማት አስወግዶ የሥራ እድል ለመፍጠር ብቃት ያለው የኤክኖሚ ሥልት አማካኝነት የኤኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ የሚያግዝ የኤኮኖሚ እቅድ በመወጠኑ ረገድ መንግሥታት እና የሥነ ኤክኖሚ ሊቃውንት በኃላፊነት መንፈስ መረባረብ እንደሚገባቸው ገልጠዋል።

በሥራ አጥነት እጅግ የተጠቃው የኅብረተሰብ ክፍል ወጣት ትውልድ መሆኑ ብፁዕነታቸው በመጥቀስ ከ 15 እስከ 24 ዓመት እድሜ ክልል የሚገኝ 78 ሚሊዮን የሚገመት ወጣት በሥራ አጥነት ችግር የተጠቃ መሆኑ በማስታወስ፣ ይኽ ደግሞ እ.ኤ.አ. በ 2010 ዓ.ም. ከጠቅላላ የሥራ አጥ ብዛት አንጻር ሲታይ 2,6 የሚሸፍን መሆኑ ገልጠው፣ በመጨረሻ ይህ የዓለም አቀፍ የሥራ እና የሠራተኛ ጉዳይ የሚከታተለው ድርጅት በቤት ሥራ የሚተዳደሩት የኅብረተሰብ ክፍል አባላት ሥራ ጉዳይ በተመለከተ የሠራተኛ መተዳደሪያ ሕግ ሥር የሚተዳደር እንዲሆን የሚያስችል ውሳኔ በማስተላለፍ እንደ ማንኛውም ሠራተኛ የሥራተኛ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ተጠብቆላቸው እንዲኖሩ የሚያበቃ ውሳኔ ያረጋገጥ ዘንድ አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.