2011-06-10 15:58:44

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ተፈጥሮን እና ሰውን የማይበክል ንጹህ የኃይል ምንጭ መርጦ መጠቀም


በቅድስት መንበር የሞልዳቪያ የኤኳቶሪያል የበሊዘ የሲሪያ የጋና እና የኔውዚላንድ ልኡካነ መንግሥታት ሆነው ከየመንሥቶታቸው የተላኩት ያቀረቡት የሹመት ደብዳቤ ትላትና ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በሐዋርያዊ መንበራቸው ተረክበው፣ ተፈጥሮ እና አካባቢ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ዓላማ ላይ ባነጣጠረ ሁኔታ ለአገልግሎት እንዲውል የሚደረገው ሩጫ ተወግዶ እንክብካቤ እና ጥበቃ RealAudioMP3 ጉዳይ ላይ ይስተዋል ዘንድ ጥሪ በማቅረብ፣ የተፈጥሮ እና አካባቢ ጥበቃ ላይ ያተኮረ ንግግር ማሰማታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ተፈጥሮን ያስረከበው ለእደ ጥበብ እድገት ቁጥጥር ሥር እንዲያውለው እና የዚህ እድገት መገልገያ እቃ እንዲሆን አይደለም፣ ስለዚህ ይኽ ግንዛቤ መንግሥታት ስለ ተፈጥሮ ጉዳይ በተመለከተ ለሚወጥኑት ለቅርብ ሩቅ እቅድ መሪ ሀሳብ እና ስለ ሕይወት እና ዕደ ጥበብ ጉዳይ በተመለከተ ለተረከቡት ኃላፊነት በጋራ ለሚያደርጉት አስተንትኖ መሠረት መሆን ይገባዋል።

ሰብአዊው ሥነ ምኅዳር እጅግ አንገብጋቢ እግብር ላይ መዋል የሚገባው ትእዛዝ ነው። ስለዚህ ተፈጥሮን የሚንከባከብ እና የሚያከብር እንዲሁም ተቀባይነት ያለው ሥነ ምርምር እና ተፈጥሮን የማይበክል የፍጥረት ሃብት የሚያከብር የሰው ልጅ ለአዳጋ የማያጋልጥ ንጹሕ የኃይል ምንጭ ለመጠቀም የሚያግዝ የሕይወት ዘይቤ መርጦ መከተል ወሳኝ ነው። ስለዚህ ይህ መመሪያ በፖለቲካው እና በኤክኖሚ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

ተፈጥሮ ለሰው ልጅ ሕይወት ኅልውና አቢይ ሚና ያለው በመሆኑም ይኽ የተፈጥሮ መሠረታዊ ዓላማ እንዳይዛባ መንግሥታት ተፈጥሮን ለመንከባከብ እና ዓላማውም እንዳይስት መረባረብ ይገባቸዋል። ለዚህ ዓይነት መሠረታዊ ሀሳብ አስተንትኖ የሚደረግበት ባህርያዊው መቀመጫ ያለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መሆኑም ቅዱስ አባታችን ዘክረው፣ ስለዚህ ይኽ ዓለም አቀፍ መንበር ለግል ጥቅም ካቀና ዓላማ ይልቅ መተባበር እና መተሳሰብ ላይ ለማነጣጠር እንዲቻል በታወረ የፖለቲካ እና የኤኮኖሚ እንዲሁም በሰልፋዊ ጭፍን አመለካከት መሠረት ዋና ዓላማው እንዲስት ማድረግ የተገባ አይደለም ካሉ በኋላ ዓለማችን የሚከተለው የልማት ዕቅድ ያስከተለው እና እያስከተለው ያለው ጉዳት እና ሁሉንም ለመቆጣጥር ያግዛል በሚባለው የእደ ጥበብ እድገት ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ለሰው ልጅ ለጥፋት እያጋለጠ መሆኑ ለሁሉም የተሰወረ አይደለም፣ እንዳውም የሰው ልጅ እቁጥጥር ሥር የሚያስገባው የእደ ጥበብ እድገት የሰው ልጅ ሰብአዊነትን ይነሳል። የእደ ጥበብ እድገት መጎናጸፍ የሚያስከትለው ትዕቢት ኅብረተሰባችንን ደረቅ የማይለወጥ የሰው ልጅ እና የተፈጥሮ ክብር ግድ የማይል ልቅ የኤኮኖሚ ሥልት እንዲከተል እና በማንኛውም ረገድ ትክክልም ይሁን የተሳሳተ መንገድ ሳይል የሚፈለገው ፍንጥዝያ ወይንም ልቅ ደስታ ነው በሚል እኔነትን ማእከል የሚያደርግ ዝግ እና ስስታም ለራስ ልቅ አሳቢነት ጠባዮች እንዲላበስ ያደረገዋል።

የሰውል ልጅ ስለ ፍትህ እና ስለ ሰላም ያለው ምኞት ማክበር አንድ ኅብረተሰብ በራስ አነሳሽነት ቤተሰብን በማክበር የኤኮኖሚ ሃብት ብቸኛ ቀዳሚነት አለው የሚለው አመለካከት የመቃወም ዓላማን ያስከትላል፣ አንድ አገር የሚኖረው ወይንም የአንድ አገር ኅልውና የሚረጋገጠው ኃላፊነት በሚገነዘበ በዜጎች የሕይወት ሙላት ነው። በሌላው ረገድ በሰው ልጅ መሆናዊው ዘንድ ያለው ወደ እውነት የማቅናት እና መልካምን የመሻት ባህርይ ለጋራ ጥምቅ መረጋገጥ የሚያግዘው ፍላጎት መሠረት መሆኑና ይህ ደግሞ ሁሉም በየፊናው ለጋራ ጥቅም እንዲጠመድ ያበረታታዋል በማለት ያሰሙት ንግግር እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.