2011-06-08 15:49:02

ታላቅዋ ብሪጣንያ፦ “አንግሊካኖሩም ኮኤቲቡስ - ለአንግሊካውያን አባላት”


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባላቸው ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣን መሰረት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እምነት በመቀበል ከኩላዊት ቤተ ክርስትያን ውህደት ለሚያደርጉ የአንጊላዊት ቤተ ክርስትያን መጋብያን (ቄሶች እና አቡናት) ጉዳይ RealAudioMP3 በተመለከተ በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የክህነት አገልግሎት እንዲፈጽሙ የሚያበቃቸው ጉዳይ በተመለከተ ያወጁት “አንግሊካኖሩም ኮኤቲቡስ - ለአንግሊካውያን አባላት” በሐዋርያዊ ሕገ መንግሥት ዘንድ የታከለው ሐዋርያዊ ሕግ በመከተል የቀድሞ 60 የአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን መጋብያን እ.ኤ.አ. ሰኔ 12 ቀን 2011 ዓ.ም. በበዓለ ጰራቅሊጦስ በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የክህነት ማዕርግ እንደሚቀበሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ቀደም ሲል ሰባት የቀድሞ የአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን መጋብያን በሶዝዋርክ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፐተር ስሚዝ እጅ ባለፈው ቅዳሜ በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የክህነት ማዕርግ መቀበላቸው ሲር የዜና አገልግሎት በማስታወስ፣ አክሎም ሌሎች አምስት ባለፈው ዓርብ በዌስትሚኒስተር በሚግኘው ካቴድራል በእንግልጣር እና ወይለስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፅዕ አቡነ ቪንሰንት ኒኮላስ እጅ የክህነት ማዕርግ እንደተቀበሉ የዜናው አገልግሎት አስታውቀዋል።

እነዚህ የካቶሊክ ቤተ ክርስያን እምነት የተቀበሉ የቀድሞ የአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን መጋብያን በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለክህነት የሚያበቃቸው እና የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ጉዳይ በተመለከተ ጥልቅ ሕንጸት እ.ኤ.አ. ከባለፈው መስከረም 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በመቀበል እና በሎንደን በሚገኘው የቸልሲ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤተ መሠረታዊ የካቶሊክ ቲዮሎጊያ ሕንጸት እንዳገኙም ሲር የዜና አገልግሎት ያመለክታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ዓመት ጥር ወር በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የክህነት ማዕርግ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀበሉት የቀድሞ የአንግሊካዊት ቤተ ክርስያን ጳጳሳት ከይዝ ኔውቶን፣ ጆን ብሮድሁርስት እና ኤንድሪው ቡርንሃም መሆናቸው የዜናው አገልግሎት በማስታወስ ገልጦታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.