2011-06-08 15:45:37

ቤተ ክርስትያን የእግዚአብሔር ኵላዊ ፍቅር መግለጫ ነች


እ.ኤ.አ. ቅዳሜ ሰኔ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን በስፐይን የዛሬ 150 ዓመት የተወለደው በኤውሮጳ ከቦታ ቦታ በመዘዋወር የሚኖረው ዘላን የኤውሮጳ ክፍለ ኅብረተሰብ አባል የእምነት ሰማዕት ብፁዕ ዘፊሪኖ ኺመነዝ ማላ ኩላዊት ቤተ ክርስትያን ብፅዕና ያወጀችለት 75ኛው ዓመት ምክንያት እና የተወለደበት 150 ዓመት ምክንያት እነዚህ በኤውሮጳ በመዘዋወር የሚኖሩት ዘላኖች RealAudioMP3 የኅብረተሰብ ክፍል አባላት በመቀበል መሪ ቃል በመስጠት የቤተ ክርስትያን ኩላዊው ፍቅር በማረጋገጥ ሐዋርይዊ ቡራእኬ እንደሚለግሱ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

በዓለም ደረጃ የእነዚህ ዘላን የኅብረትሰብ ክፍል አባላት ብዛት በጠቅላላ 36 ሚሊዮን የሚገመት ሲሆን፣ ከዚህ ብዛት ውስጥ 18 ሚሊዮን የሚገመተው በህንድ፣ 15 ሚሊዮን ደግሞ በኤውሮጳ 2 ሚልዮን የሚገመተው ደግሞ በላቲን አሜሪካ የሚኖር ሲሆን፣ በኢጣሊያ 170 ሺህ እንደሚገመቱ ለማወቅ ሲቻል፣ ጳጳሳዊ የስደተኞች እና የተጓዦን ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ከኢጣሊያው ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው ጽ/ቤት፣ ከሮማ ሰበካ እና ከቅዱስ ኤጂዲዮ የካቶሊክ ማኅበረሰብ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው መንፈሳዊ መርሃ ግብር መሠረት የዚህ የዘላኖች ኅብረተሰብ ክፍል አባላት በቅዱስ ጴጥሮስ መንፈሳዊ ንግደት በመፈጸም ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጋር እንደሚገናኙ ተገልጠዋል።

የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበረሰብ ሊቀ መንበር ፕሮፈሶር ማርኮ ኢምፓሊያዞ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ እነዚህ የኤውሮጳ ዘላን የኅብረተሰብ ክፍል የሆኑት በጠቅላላ የሮም የሲንቲ የማኑከስን የካለን የኒሽን ዘላን ጎሳዎች የሚወክሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ ትሩፋት በሚገኝበት ቅዱስ ሥፍራ መንፈሳዊ ንግደት ሲያከናውኑ እና በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቀባበል ተደርጎላቸው መሪ ቃል ሲቀበሉ ይህ እፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. የሚፈጸመው መንፈሳዊ ንግደት በዓይቱ ቀዳሜ መሆኑ አስታውሰው፣ እነዚህ አናሳው የኤውሮጳው ክፍለ ኅብረተሰብ ዘላን ማኅበርሰብ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ተጠብቆለት ተከብሮ እንዲኖር ጥሪ የሚያቀርብ መርሃ ግብር ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት እነዚህ የኤውሮጳ ዘላን ክፍለ ኅብረተሰብ በተለያዩ የኤውሮጳ አገሮች ተዋህደው መኖር እንደጀመሩ ፕሮፈሰር ኢምፓሊያዞ ገልጠው፣ ቤተ ክርስትያን እነዚህን ልጆችዋ በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አማካኝነት ተቀብላ ይኸንን ተዋህዶ ለመኖር የተጀመረው መልካም ሂደት በማጽናት እና ብሎም በማበረታታት፣ በዚሁ ጉዳይ ቤተ ክርስትያን ከጥንት ጀምራ ይኸንን ዘላን የኅብረሰብ ክፍል ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ተጠብቆለት እንዲኖር እና ተዋህዶ ለመኖር የሚያስችለው መርሃ ግብር በሁሉም አገሮች ዘንድ በማነቃቃት በቅድሚያ በማስተናገድ እና ለዚህ የህብረተሰብ ክፍል ተገቢ ሥፍራ ለመስጠት የተገባ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በመወጠን የተሟላ ሕንጸት እንደምትሰጥ በማረጋገጥ፣ ይኸንን መንፍሳዊ ንግደት የሚመሩ የስደተኞች እና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ ሲሆኑ፣ ብፁዕነታቸው እነዚህ የኤውሮጳ ዘላን የኅብረሰብ አባላትን በቅዱስ አባታችን ፊት በማቅረብ በሚያሰሙት ንግግር ቤተ ክርስትያን ለዚህ የኅብረተሰብ ክፍል የምትሰጠው መንፈሳዊ እና ሰብአዊ አገልግሎት ምን እንደሚመስል እንደሚገልጡ ፕሮፈሰር ኢምፓሊያዞ ከወዲሁ ገልጠዋል።

በመጨረሻም ፕሮፈሶር ኢምፓሊያዞ እነዚህ ዘላን የኤውሮጳ ክፍለ ኅብረተሰበ የናዚው ሥርዓት በሰው ዘር ላይ የፈጸመው ዕልቂት ሰለባ በመሆን በአውሽዊዝ በቢርከናው እና በበርገን ቤሰን ለጅምላዊ ግድያ ማጎሪያ ሠፈር ተዳርገዋል። ይኸንን በማስታወስ ከዚህ የአረመኔው የናዚው የጅምላዊው ግድያ ውሳኔ የተረፉት በማጎሪያው የዕልቂት ሠፈር ገና የ 9 ዓመት እድሜ እያሉ ከሌሎች 200 የዘላን ቤተሰብ አባላት ጋር የተጎሳቆሉት ካቶሊክ ምእመን የዚህ የዘላን ኅብረተሰብ ክፍል አባል የዕድሜ ባለ ጸጋ ሰይጃ ስቶይካ ከቅዱስ አባታችን ጋር በሚካሄደው ግኑኝነት ምስክርነት እንደሚያሰሙ በመግለጥ፣ በኤውሮጳ ተዋህዶ ለመኖር የሚያግዝ ለስደተኞች እና ለዘላኖች ጥቅም ያቀና በመተዋወቅ ተዋህዶ ለመኖር የሚያግዝ መርሃ ግብር እየተወጠነ ነው። ስለዚህ የማስተናገድ እና ተዋህዶ የመኖር አስፈላጊነቱ ግንዛቤ በኤውሮጳ ዜጎች እየጎላ መሆኑ ፕሮፈሶር ኢምፓሊያዞ በማብራራት፣ ቤተ ክርስትያን እነዚህን የኤውሮጳ ክፍለ ኅብረሰብ የሆኑት ዘላን አባላት በመቀበል የምትሰጠው ግልጋሎት ለኤውሮጳ መንሥታት እና በጠቅላላ ለዓለም መንግሥታት አብነት ነች። ቤተ ክርስትያን ማንንም አታገልም እንዳው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እንዳሉት የእግዚአብሔር ኵላዊ ፍቅር መግለጫ ነች በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.