2011-06-06 14:37:18

አባ ሎምባዲ፦ የክሮአዚያ ሕዝብ ካለው ጥልቅ እምነት ለይቶ መረዳት የሚቻል አይደለም


የቅድስት መንበር የዜና እና ኅትመት ጉዳይ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛው የክሮአዚያዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማሰመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በቅድሚያ የክሮአዚያ ሕዝብ እና መንግሥት ለቅዱስ አባታችን ያደረገው አቀባበል እና ያሳየው ፍቅር ካሰመሩበት በኋላ፣ ከባህል ሊቃውንት ጋር የተደረገው የግኑኝነት RealAudioMP3 መርሃ ግብር ያዘጋጁት የባህል ሊቃውንት ይኸንን ግኑኝነት ሲያስጀምሩ እና ሲያስተዋውቁ የክሮአዚያው ታሪክ እና ባህል ከክርስትናው ባህል ጋር የተቆራኘ የማይነጣጠል በመሆኑ አለ ክርስትናው ታሪክ የክሮአዚያ ባህል ለመረዳት የማይቻል መሆኑ እንዳሰመሩበት አባ ሎምባርዲ ገልጠው፣ ሰለዚህ ከእምነት እና ከካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ታሪክ ውጭ የክሮአዚያ ታሪክ ለመረዳት እና ወይንም ለመጻፍ የሚቻል አይደለም ካሉ በኋላ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከክሮአዚያ ወጣቶች ጋር በመገናኘት የሰጡት መሪ ቃል፣ የቀረበው መዝሙር የተፈጸመው ጸሎት እና በአደባባዩ በቅዱስ ቁርባን ፊት የተካሄደው የአስተንትኖ ጸሎት በእርግጥ በተዛማጅ ባህል በተጠቃችው አገር ዋናው አደባባይ በቅዱስ ቁርባን ፊት የጸሎት አስተንትኖ ሲፈጸም ማየቱ የሚያስደንቅ ብቻ ሳይሆን ባንድ ትልቅ አደባባይ የዚህ አይነቱ ጥክቅ መንፈሳዊ ክንዋኔ ሲፈጸም ለመገመቱ ያዳግታል።

ክሮአዚያ እንደ ማንኛውም የኤውሮጳ አገር በተዛማጅ ባህል የተጠቃች ብትሆንም ቅሉ ይኸንን ተጋርጦ በመግጠም ጥልቅ መለያዋ የሆነው ክርስትና እና ካቶሊካዊነት አጅግ አስፈላጊ መሆኑ የተመሰከረበት እና ይኽ እውነት ዳግም ያነቃቃ ሓዋርያዊ ጉብኝት ነው። ቅዱስ አባታችን የዚያች አገር የቤተሰብ አባል በመሆን የእምነት የባህል ልብ ምታት ቀርበው በመለየት እና የራሳቸው በማድረግ የሕዝቡን ጉዞ በመደገፍ እና በጸሎት ቅርብ በመሆን ከሁሉም ከክሮአዚይ ብፁዓን ጳጳሳት ከዓለማውያን ምእመን ከምሁራን አካላት ከወጣቱ የአገሪቱ ክፍለ ኅብረተሰብ ጋር በመገናኘት በሰጡት መሪ ቃል እንደመሰከሩት አባ ሎምባዲ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.