2011-06-06 14:34:47

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ ዓለምን እንደ ፈጣሪ ፈቃድ ለመለወጥ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ከባለፈው ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን እስከ እሁድ ሰኔ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. በክሮአዚያ ሐዋርያዊ ጉብኝት ማካሄዳቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ይኸው ቅዱስነታቸው ቅዳሜ ወደ ክሮአዚያ ለዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለመነሳት በአሮፕላን ውስጥ እያሉ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው መጠይቅ ሲመልሱ፣ በቅድሚያ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ RealAudioMP3 በክሮአዚያን ያካሄዱት ሶስቴ ሐዋርያዊ ጉብኝት ከዚህ አኳያ ሲታይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሚፈጽሙት ሐዋርያዊ ጉብኝት በቅድስት መንበር እና በክሮአዚያ መካከል ያለው ጥብቅ ቅርርብ እና ወዳጅነት የሚገልጥ ከመሆኑም ባሻገር፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ገና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከመሾማቸው በፊት፣ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የአንቀጸ ሃይማኖት ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ እያሉ ያችን አገር ሁለቴ እንደጎበኙ እና ከሳቸው በፊት ዓለም አቀፍ የቲዮሎጊያ ድርገት ሊቀ መንበር ብሎም የዚህ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ በመሆን ያገለገሉ ካርዲናል ብፁዕ ሰፐር በማስታወስ፣ አንዱ የዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ምክንያት ለእኚህ አቢይ የእምነት አብነት ደስተኛ ርህሩህ አስተዋይ የእምነት ቀናተኛ የሆኑት ታላቅ ካርዲናል ብፁዕ ሰፐር ቅዱስ ትሩፋት ፊት ለመጸለይ የክሮአዚያ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያንን የምትኖረው ክርስትያናዊ ሰብአዊነት መልእለተ ባህርይ መግለጫ የሆነው ሕዝባዊው የእምነት ተግባር በጠቅላላ የምትኖረው ተጨባጭ እና ሥጋ ለበስ እምነት ለማበረታታ እና በቅድስት መንበር እና በክሮአዚያ መካከል ያለው የጠበቀው ግኑኝነት ለመመስከር ነው።

ክሮአዚያ ሩቅ ባልሆነ የጊዜ ገደብ ውስጥ የኤወሮጳ ኅብረት አገሮች አባል እንደምትሆን ሲገለጥ ሆኖም ግን የክሮአዚያ ሕዝብ በኤውሮጳ ኅብረት ላይ መጠራጠር ያለው ቢመስልም፣ ክሮአዚያ እና ሕብዘ ክሮአዚያ ኤውሮጳዊ ነው ካሉ በኋላ፣ ብዙውን ጊዜ ብፁዕ ካርዲና ሲፓክ፣ ብፁዕ ካርዲናል ኩሃሪች እና ብፁዕ ካርዲናል ቦዛኒች በተጋጋሚ ክሮአዚያ እና ሕዝባዋ ሚተለ ኤውሮጵውያን እንጂ ባልካናውያን እንዳልሆነ ነው የገለጡልኝ፣ ስለዚህ ሕዝቡም ሆኖ ባህሉ ኤወሮጳውነት ማእከል ያለው ነው። ስለዚህ ይኸንን አመክንዮ መሠረት በማድረግ ብቻ አገሪቱ የኤውሮጳ ኅብረት አባል መሆን ይገባታል ብለዋል። የክሮአዚያ ሕዝብ በኤውሮጳው ኅብረት መዋቅር ላይ ያለው መጠራጠር በኅብረቱ ዓለማ ላይ አይተማመንም ማለት ሳይሆን፣ ኅብረቱ የሚያጎላው ቢሮክራሲያዊ የሥልጣን ማእከላዊነት ላይ ያተኮረ መጠራጠር ነው፣ ክሮአዚያ የኤውሮጳ ኅብረት አገሮች አባል መሆን ክርስትያናዊ መሠረት ላለው ለኤውሮጳው ባህል አቢይ ድጋፍ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ካርዲናል ብፁዕ ስተፒናክ አቢይ እረኛ አቢይ ክርስትያን፣ ክርስትያናዊ ሰብአዊነት የኖረ ኢሰብአዊነት ተግባር እና አመለካከቱንም ጭምር ፊት ለፊት የገጠመ በይፋ በእምነት እና በባህል ደርጃ የተቃወም፣ የዚህ ኢሰብአዊ ባህል መሠረተ ቢስነቱን የመሰከረ፣ የቤተ ክርስትያን ልጅ ዘክረው በመጀመሪያ የኡስታሳው ፈላጭ ቆራጭ መንግሥት ከዛም በኋላ የናዚውን አረመኔው መንግሥት፣ በግልጽ ሰብአዊነት የተካነው ባህል በማጉላት በግልጽ የተቃወመ ብሎም የኮሙኒዝም ሥርዓት ባንሠራፋበት ወቅት ኢእግዚአብሔርነት/እግዚአብሔር የለም የሚለውን ባህል ክርስቶስ ማእከልነት ያለው እውነተኛው ሰብአዊነት በመመስከር፣ ለክሮአዚያ ብቻ ሳይሆን ለመላ ሕዝብ የእምነት አብነት የሆነው የቤተ ክርስትያን ልጅ አማካኝነት ከክሮአዚያ ሕዝብ ጋር በመሆን እግዚአብሔርን ለማመስገን ያቀደ ሐዋርያዊ ጉብኝት ነው ካሉ በኋላ፣ ክሮአዚያ እምነት በልብ የምትኖር መጪውን በደስታ የምትመለክት አገር ነች እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.