2011-06-03 13:55:43

በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ያነቃቃው ስብሰባ


እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 16 እስከ ነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. በማድሪድ ከተማ የሚካሄደው 26 ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ምክንያት በማድረግ በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ቢሮ ስለ ወጣት RealAudioMP3 ጉዳይ እና በየዓመቱ በእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን አዘጋጅነት የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ዋና ዓላማው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው አስተዋጽእ ለማሳወቅ ያቀደ ዓውደ ጥናት መካሄዱ ሲገለጥ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ፍራንሲስ አሲዚ ቹሊካት በተካሄደው ዓወደ ጥናት ባሰሙት ንግግር የሕይወት ባህል የሚያነቃቃ፣ ሕይወት በሁሉም ደረጃ ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት እንዲከበር የሚለው የላቀው እሰይታ ማእከል ያደረገ ይኸንን እሰይታ የሚያነቃቃ እና መሠረታዊ አመክንዮውን የሚያስተጋባ የጥናት ጽሑፍ፣ መዝሙር ቅብ እና ንድፍ አማካኝነት ከ 16 እስከ 30 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የሚያሳትፍ የባህል ውድድር እንደሚካሄድ ማሳወቃቸው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰኘው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.