2011-06-01 11:58:44

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮ (01.06.2011)


ኦሪት ዘፀአት 32፡11 ‘ሙሴም በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት ጸለየ፥ አለም። አቤቱ፥ ቍጣህ በታላቅ ኃይልና በጽኑ እጅ ከግብፅ ምድር ባወጣኸው በሕዝብህ ላይ ስለ ምን ተቃጠለ? ግብፃውያንስ። በተራራ መካከል ሊገድላቸው፥ ከምድርም ፊት ሊያጠፋቸው ለክፋት አወጣቸው ብለው ስለ ምን ይናገራሉ? ከመዓትህ ተመለስ፥ ለሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ። ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ ይህችንም የተናገርኋትን ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፥ ለዘላለምም ይወርሱአታል ብለህ በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምንና ይስሐቅን እስራኤልንም አስብ። እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው ክፋት ራራ።’ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ ስለ ክርስትያን ጸሎት የጀመርነውን ትምህርተ ክርስቶስ በመቀጠል ዛሬ ስለ ታላቁ የትንቢት ኣባት ስለ ሙሴ እንመለከታለን። ሙሴ በእግዚአብሔርና በእስራኤል ሕዝብ መካከል ኣስተራቂ በማገልገሉ የኣማላጅነት ጸሎት ጥሩ ኣብነት ነው። ሲነበብ በሰማነው የቅዱስ መጽሓፍ ክፍል በኦሪት ዘፀኣት 32 ላይ ሙሴ ወደ ደብረሲና ተራራ ወጥቶ ስለሕዝቡ ጸሎት ኣሳርጎ እግዚአብሔር የሰጠውን የሕግ ጽላት ይዞ ሲወርድ ሕዝቡ እምነት ኣጉድሎ የጥጃ ጣዖት ሰርተው ሲዘፍኑና ሲያመልኩ ባየ ግዜ እጅግ ኣዘነ፤ የእግዚአብሔር ቁጣም ወዲያውኑ ታየው። የኃጢኣታቸው ክብደት ቢያውቅም ሙሴ ገና ለሕዝቡ ከእግዚአብሔር ምህረት ለመነ፤ እግዚአብሔርን የሕዝቡን ኃጢኣት ይቅር እንዲልና ኣዳኝ ኃይሉን እንዲያሳያቸው ተማጠነ። የሙሴ ጸሎት ራሱ እግዚአብሔር ሕዝቡ እንዲድኑ ያለው ፍላጎትንና ለኪዳኑ ታማኝ መሆኑን የሚገልጥ ነው። ሙሴ ስለ ሕዝበ እስራኤል ሲያማልድ እግዚአብሔርንና ምሕረቱን ጠለቅ ባለ መንገድ በማወቅ ራስን ለሌሎች መሥዋዕት እስከ መስጠት በሚያስችል ፍቅር ለማፍቀር ችለዋል። በዚህ ጸሎት ሙሴ ከርሱ ባሻገር ለሚመጣው ፍጹም ኣስታራቂ ለሆነው ለእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስን ያመለክታል። ኢየሱስ ይህን ኣስተራቂነት ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች እንዲታረቁና ኃጢኣታቸው ይቅር እንዲባልላቸው በደሙ ኣዲስና ዘለዓለማዊ ኪዳን ኣቆመ።







All the contents on this site are copyrighted ©.