2011-06-01 14:16:16

አይቨርይ ኮስት፦ ተፈናቃዮች መልሶ ማቋቋም


በብዛት የአይቨሪይ ኮስት የቀድሞ ርእሰ ብሔር ግባግቦ ደጋፊ የጉዌረ ጎሳ አባላት የሚገኙባቸው በዱኤኩኤ ቁምስና መጠለያ አግኝተው በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እርዳታ ሥር በመተዳደር ላይ የሚገኙት 27 ሺህ RealAudioMP3 ተፈናቃዮች መልሶ ለማቋቋም እንዲቻል የማን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጋስፓርድ በብይ ኜባ ለመንግሥት እና ለተባበሩት መንግሥታት ጥሪ ማቅረባቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

እነዚህ ባለፈው መጋቢት ወር 2011 ዓ.ም. በአገሪቱ በተካሄደው የርእሰ ብሔር ምርጫ ያሸነፉት የርእሰ ብሔር ኡታራ ደጋፊዎች የረፓብሊክ አይቨሪይ ኮስት የመከላከያ ኃይል አባላት አገሪቱን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠሩ በኋላ የተፈናቀሉት የቀድሞ የአገሪቱ ርእስ ብሔር ግባግቦ ደጋፊዎች በተባበሩት መንግሥታት ልኡካን አማካኝነት የጸጥታ እና የሰላም ዋስትና አግኝተው ለመኖር የሚያስችላቸው ሁኔታ ተረጋገጦላቸው የምግብ እርዳታ እና የጤና ጥብቃ አገልግሎት ድጋፍ እንዲያገኙ ብፁዕ አቡነ ጋስፓርድ በብይ ኜባ ጥሪ በማቅረብ በአገሪቱ አሁንም አለመረጋገት በስፋት እንደሚታይ ገልጠው፣ የተፈናቀሉት ቤት እና ንብረታቸው ያጡት ዳግም ለማቋቋም የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ትብብር ወሳኝ ነው እንዳሉ ፊደስ የዜና አግልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.