2011-05-30 14:17:05

ጳጳሳዊ የግረጎሪያና መንበረ ጥበብ፦ እምነት እና ሥነ ምርምር


እ.ኤ.አ. መጋቢት 2009 ዓ.ም. የሕይወት አመጣት በተመለተከተ እ.ኤ.አ. በ 1859 ዓ.ም. ቻርለስ ዳርዊን ያቀረበው የዝግመተ ለውጥ መላ ምት 150ኛው ዓመት ምክንያት፣ የሥነ ሕይወት ዝግመተ ለውጥ፣ ተግባራዊው እና ሥነ ሐሳባዊው መግለጫው በሚል ርእስ ሥር በጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ ዓለም አቀፍ ዓውደ ጥናት መካሄዱ የሚዘከር ሲሆን፣ RealAudioMP3 የዚህ ዓወደ ጥናት ጠቅላይ ሰነድ ለንባብ መብቃቱ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቤተ ክርስትያን ቻርለስ ዳርዊንን አላወገዘችም። ያቀረበው የሥነ ሕይወት ዝግመተ ለውጥ መላ ምትም ሳይቀር እንዳልኮነነች የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ የጥናቱ ሰነድ ለንባብ በበቃበት ጉባኤ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር በማስታወስ፣ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እምነት እና ምርምር በሚል ርእስ ሥር በደረሱት ዓዋዲ መልእክት አማካኝነት የገለጡት በእምነት እና በምርምር መካከል ያለው የዕይታ እና ሥረ ነገራዊ ትስስር በመመስከር በተለያዩ የሥነ ምርምር እና የጥናት ዘርፎች መሠረት በእምነት እና በሥነ ምርምር መካከል ያለው ግኑኝነት መገለጥ አለበት። ምክንያቱም እምነት ምርምርን ምርምር እምነትን አያገልም ካሉ በኋላ፣ ብዙዎች አሁንም ቢሆን እምነት እና ሥነ ምርምር ተቃራኒ የሚገፋፉ አንዱ ሌላውን የሚያገል እንደሆነ አድርገው የሚመለከቱ የሥነ ምርምር አካላት እንዳሉ አስታውሰው፣ ሥነ ምርምር በራሱ ላይ የተዘጋ እኔ ለገዛ እራሴ በቂ ነኝ የሚል ሳይሆን፣ ክፍት ነው ሲሉ፣ ሰነዱ ለንባብ ለማቅረብ በተካሄደው ጉባኤ ንግግር ያሰሙት የሥነ ምርምር ሊቃውንት አውለታ፣ ለክለርክ እና ማርቲነዝ በታሪክ የሚገለጠው በእምነት እና በምርም መካከል ያለው ግጭት እና ልዩነት ርእዮተ ዓለም መሠረት ያደረገ እንጂ መሆናዊ እና ቅርጻዊ መሠረት እንደሌለው በተለያየ የጥናት ዘርፍ ሥር በጥልቅ ማስረዳታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.