2011-05-30 14:13:58

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ካቶሊክ መሆን ማለት ማርያማዊ መሆን ማለት ነው


ከትላንትና በስትያ ጧት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ አንዳንድ የራቲስ ቦና ማርያማውያን የካህናት ማኅበር አባላት ተቀብለው መሪ ቃል ሲሰጡ፣ ቅዱስነታቸው ገና ከሕጻንነታቸው ጀምረው በተለይ ደግሞ የአስራ አራት ዓመት እድሜ ታዳጊ ወጣት እያሉ በሰፊው የኤውሮጳው ክልል የሂትለር ፈላጭ ቆራጭ መንግሥት ይገዛበት በነበረበት ወቅት በኤወሮጳ RealAudioMP3 የክርስትናው መንፈስ ኅልውናው ላደጋ ያጋለጠ እንዳውም ጨርሶ እንዳይኖር የሚያደርግ ተመስሎ በታየበት ወቅት ማርያም የሁሉም ደጋፊ በመሆን ይህች የእምነት አብነት የሆነቸው እናት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛውን መንገድ በማመልከት በእርሱ እንድንጸን ደግፋናለች ብለዋል።

ሂትለር ፖላንድ ቀጥሎም ዴንማርክ በልጅም ሆላንድ ሉሰንበርግ ፈረንሳይን የቀድሞ ዩጎስላቪያን ግሪክን በመቆጣጠር የኤውሮጳ ክርስትያናዊ ባህል እና እምነት በማናጋት ኅልውናው እጥያቄ ውስጥ በማስገባት ቀጥሎ ወታደራዊ ኃይሉ ወደ ሩሲያ እንዲያቀና በማድረግ ማርያማውያን የካህናት ማኅበር እንዲበታተን ያደረገ ቢመስልም፣ ቅድስት ድንግል ማርያም ኃይል ከሆነው ኃይም በመማጠን መልካም የሆነው ሁሉ ቀጣይነቱ በማረጋገጥ ህዝብን በመደገፍ ያንሰራፋ ከነበረው ከጨለማው ኃይል እንድንላቀቅ አድርጋናለች፣ ሰለዚህ የክርስትናው እምነት የማርያም ድጋፍ የተከተለው መሆኑ አብራርተው አለ መርያም የክርስትናው እምነት መግለጡ ያዳግታል ብለዋል።

በወቅቱ የሥነ ማርያማዊ ጥናት ተለይቶ በማርያም እምነት ላይ ያተኮረ እንዲሆን ለዚህ ልዩ የቲዮሎጊያ ክፍለ ጥናት ፈር እንዲይዝ ማድረጉንም አስታውሰው፣ ቅድስት ኤልሳቤጥ ለማርያም በማመንሽ ምንኛ የታደልሽ ነሽ በማለት በማርያም ያለው እምነት እና የማርያም እምነት ታላቅነት እና ጥልቀቱንምን ጭምር በማጉላት፣ ማርያም በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የአብርሃም የተስፋውን እምነት ገቢራዊ አድርጋለች፣ ስለዚህ የእምነት አብነት ነች፣ በእርስዋ አማካኝነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማወቅ እና ማፍቅረን እንማራለን፣ ከዚህ በመቀጠለም ላላወቁት ለማሳወቅ በአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ እንሳተፋለን ካሉ በኋላ፣ በክርስትናው ባህል በቤተ ክርስትያን እና በእያንዳንዱ ክርስትያን ሕይወት የማርያም ሥፍራ ምን መሆኑ በማስረዳት የሰጡት መሪ ቃል አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.