2011-05-25 16:59:31

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮ (18.05.2011)


ኦሪት ዘፍጥረት 32፡24~30 ‘ያዕቆብ ግን ለብቻው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር። እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ ነካው፤ ያዕቆብም የጭኑ ሹልዳ ሲታገለው ደነዘዘ። እንዲህም አለው። ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ። እርሱም። ካልባረክኸኝ አልለቅቅህም አለው። እንዲህም አለው። ስምህ ማን ነው? እርሱም። ያዕቆብ ነኝ አለው። አለውም። ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና። ያዕቆብም። ስምህን ንገረኝ ብሎ ጠየቀው። እርሱም። ስሜን ለምን ትጠይቃለህ? አለው። በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም። እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው። ጵኒኤልንም ሲያልፍ ፀሐይ ወጣችበት፥ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር።’
ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ ስለክርስትያን ጸሎት በተከታታይ በምናደርገው ትምህርተ ክርስቶስ ዛሬ ትላላቅ ኣበውና ጸሎታቸው በመጽሓፍ ቅዱስ እንመለከታለን። በኦርቲ ዘፍጥረት 32፡23~33 እንደተመለከተው ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ያደረገውን ትግል እንመለከተለን። ይህ ምሥጢራዊ ግኑኝነት በሌሊት ነው የተፈጸመው፤ ሁኔታውም እንዲህ ነበር፤ ያዕቆብ ብቻውንና ኣለምንም የመከላከያና የመዋግያ ትጥቅ ነበር፤ ይታገለው የነበረ በመጨረሻም ያሸነፈው ማን መሆኑ በመጀመርያ ግልጽ ኣይደለም። ያዕቆብ ቆስለዋል፤ ሽንፈቱን በመቀበል ለተፎካካሪው ስሙን መግለጥ ኣለበት፤ ሆኖም ግን እስራኤል የሚለው ኣዲስ ስም እና ቡራኬ ይቀበላል። ጎህ በቀደደ ግዜ ያዕቆብ ከእርሱ ጋር ሲታገል ያደረው እግዚአብሔር መሆኑን ያውቃል፤ እያነከሰም ጵኒኤልን ተሻግረዋል። የቤተ ክርስትያን መንፈሳዊ ጉዞ ይህን ታሪክ በልበ ምሉነትና በእምነት የሚደረገው የጸሎት ትግል ምልክት ትለዋለች፤ ይህ ዓይነት ጸሎት ነፍስ ተቸግራ በጨለማ በምትገኝበት ግዜ መጽናት እንዳለብን የሚጠራ በመጨረሻም በውስጣዊ ህዳሴና በእግዚአብሔር ቡራኬ እንደሚሸለም ያመለክታል። ይህ ትግል የማይታክት ጥረታችን ይጠይቃል፤ በመጨረሻም ለእግዚአብሔር ምሕረትና ጸጋ እጃችን በመስጠት በድል ይደመደማል። ጎህ ሲቀድ ያዕቆብ የትግሉን ቦታ ጵኒኤል ብሎ ሰይሞታል፤ ትርጉሙም የእግዚአብሔር ገጽ ማለት ነው፤ ለዚህም ነው በመጨረሻ ‘እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች’ ያለው። በምናሳርገው ጸሎት የእምነት ሠናይ ገድል ስናደርግ ሊረዳን እንዲሁም ፊቱን ለማየት በፍላጎት ስንቃጠል ሊባርከን እንለምነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.