2011-05-23 13:21:09

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ ጸሎት በቻይና ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቻይና ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና ለስቃይ እና መከራ ተጋልጠው የሚገኙት የቻይና ምእመናን ሁሉም ምእመናን በጋራ እንዲጸልዩ ያቀረቡት ጥሪ በመላ ዓለም በሚገኙት ካቶሊክ ቤተ ክርስያን ማስተጋባቱ የቅድስት መንበር የዜና የማሥተም ክልፍ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምንት ማገባደጃ በቻይና ለምተገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እንዲጸለይ የቅዱስ አባታችን ጥሪ በሚል ርእስ ሥር ባቀረቡት የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ በመግልጥ፣ RealAudioMP3 የቻይና ካቶሊክ ምእመናን በቅድስት ድንግል ማርያም ላይ ያላቸው ጽኑ አክብሮት በሻንጋይ የሚገኘው የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሥፍራ የሚመሰክረው መሆኑ በመዘከር፣ ይኸንን ምክንያት በማድረግ ቅዱስነታቸው ነገ ማክሰኞ በላቲን ሥርዓት በሚከበረው የቅድስት ድንግል ማርያም ረዳኢተ ክርስትያን ዓመታዊ በዓል በመላ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በቻይና ስለ ምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የጸሎት ሐሳብ እንዲሆን ያስተላለፉት ውሳኔ ተግባራዊ እንደሚሆን አባ ሎምባርዲ ባቀረቡት ርእሰ አንቀጽ አስታውቀዋል።

እ.ኤ.አ. ግንቦት 24 ቀን የረዳኢተ ክርስትያን ዓመታዊ በዓል ምክንያት ቅዱስ አባታችን በቻይና ስለ ምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በኵላዊት ቤተ ርክስትያን የጸሎት ሐሳብ እንዲሆን ያስተላለፉት ውሳኔ፣ ቅዱስነታቸው ጸሎት ኃይል መሆኑና የጸሎት ኃይል ላይ ያላቸው ጥልቅ እና ጽኑ የምነት የሚመሰክር መሆኑ አባ ሎምባርዲ በማብራራት፣ የዛሬ 20 ዓመት በፊት አባ ሎምባርዲ በቻይና ከአገሪቱ ውሉደ ክህነት አባላት ጋር በመሆን መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው እንዳበቁ አንድ ቻይናዊ በእድሜ የገፉ ካህን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ቅዱስ አባታችን ደህና ናቸው ወይ በማለት ያቀረቡልኝ ጥያቄ፣ በአገሪቱ የሚገኘው ካቶሊክ ምእመን እና ውሉደ ክህነት ከመንበረ ከቅዱስ ጴጥሮስ በተለያየ ምክንያት ካለ ገዛ እራሱ ፈቃዱ እንዲገለል ቢገደድም በልባቸው እና በቤተ ክርስትያናቸው ለጴጥሮስ ተከታይ ያላቸው ታማኝነት ፍቅር እና አክብሮት ታዛዥነት አቅበው ይኸንን በመመክሰር መሥዋዕትነት የከፈሉ እና የሚኖሩ በጠቅላላ ከቅዱስ አባታችን እና ከሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በጸሎት በውህደት እንደሚኖሩ ለማረጋገጥ ችያለሁ።

ቅዱስ አባታችን በረዳኢተ ክርስትያን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በቻይና ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እንዲጸለይ ስለ ቻይና የጸሎት ቀን ወስነው በቻይና የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና ምእመናን እንዲጸለይ በቻይና የምተገኘው ካቶሊክ ቤተ ክስትያን እና ምእመናን መብት ነው። በቻይና ብሔራዊ ካቶልክ ቤተ ክርስትያን በሚል መጠሪያ ከእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የተነጠለቸው እና ከመንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ውህደትዋን አቅባ የምትኖረው ለስቃይ እና መከራ የተጋለጠቸው በቻይና የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በመጸለይ የቤተ ክርስትያን ውህደት እንዲታቀብ ሁሉም ካቶሊክ ምእመን በርትቶ እንዲጸልይ የሚያሳስብ ጥሪ ነው በማለት ርእሰ አንቅጹን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.