2011-05-23 16:02:17

የር.ሊ.ጳ የጸሎተ ንግሥተ ሰማያት ኣስተምህሮ (22.05.2011)


ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ የዛሬ እሁድ ከትንሣኤ በኋላ ኣምስተኛ ሆኖ የዕለቱ ወንጌል ‘ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።’ በማለት ዕጥፍ እምነት እንዲኖረን ያዛል፤ በእግዚአብሔርና በኢየስይስ ማመን እንዳለብን ያሳስበናል። እነኚህ ሁለት የተለያዩ እምነቶች ኣይደሉም፤ ኣንድ የእምነት ተግባር በመሆን በሙሉ ልባችን በኣንድያ ልጅ ኣማካኝነት ለተሰጠን የደህንነት ተግባር ኣለመጠየቅ መቀበል ኣለብን። ኣዲስ ኪዳን የማይታየውን እግዚአብሔር እንዲታይ ኣደረገ፤ በዛሬው ወንጌል፤ ‘ፊልጶስ። ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል አለው። ኢየሱስም አለው። አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ። አብን አሳየን ትላለህ? እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን?’ ባለው መሠረት ኢየሱስን ያየ እግዚአብሔር ኣብን እንዳየ በመመስከር እግዚአብሔር ፊቱን እንዳሳየን ይገልጣል። ወልደ እግዚአብሔር በምሥጢረ ሥጋዌ በሞቱና በትንሣኤው ከኃጢኣት ባርነት ነጻ በማውጣት የእግዚአብሔር ልጆች የምንሆንበት ነጻነት በመስጠት የእግዚኣብሔር ገጽታ ፍቅር መሆኑን ኣሳወቀን፤ እግዚአብሔርን ማየት ይቻላል፤ በክርስቶስ መታየት ችለዋል። የኣቪላዋ ቅድስት ተረዛ ‘መልካም ነገሮቻችን በሚያቆመውና የደኅንነት ዋስትና ከሚያቆመው ከቅዱሱ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰብ ኣውነት መራቅ የለብንም’ ስትል እንደ እኛ ሰው በመሆን እግዚአብሔር ኣብን ያሳየንና የገልጠልን የጌታ ቅዱስ ሰብ ኣውነት መራቅ እንደሌለብን ታሳስበናለች። ስለዚህ ሓዋርያት እኛም ከእርሳቸው ጋር ነን፤ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመንና ከእርሱ ጋር ኣንድ ሆኖ በመኖር የጌታን ዘለዓለማዊ ተግባር በታሪክ ሊፈጽሙ ይችላሉ። ለዚህም ጌታ ኢየሱስ በዮሐ.14፡12 ‘እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥’ በእርሱ በማመን የደኅንነት ተግባሩን ለሚያራምዱ ምን ዓይነት ችሎታ እንደሚሰጣቸው ይገልጣል።

በኢየሱስ ማመን ማለት በየዕለቱ በምንደርጋቸው ተግባሮቻችን እርሱን መከተል እንዳለብን ያመለክታል። ባለናዝሬቱ ኢየሱስ በሚለው ሁለትኛ መጽሓፌ ገጽ 306 ላይ ይህንን ሳብራራ፡ ‘ትሕትና በተሞላበት ሁኔታ መሥራት የእግዚአብሔር ምሥጢር ጠባይ ነው፤ ቀስ በቀስ ትልቁ የሰው ልጅ ታሪክ ይገነባል፤ እንደኛ ሰው ሆነ፤ ሆኖም ግን በግዜው በነበሩ ሰዎች በተለይም በባልሥልጣናት ያልታወቀ ነበረ፤ ታሞ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሣ፤ በተገልጠላቸው ሰዎች እምነት ኣማካኝነት ለሁሉም የሰው ልጆች ለመድረስ ፈለገ፤ እርሱ ትሕትና በተሞላበት መንገድ ዘወትር የልቦቻችን በሮች ያንኳኳል የከፈትንለት የሆነ እንደሆነ ቀስ በቀስ ዓይኖቻችን በመክፈት ለማየት ያስችለናል’ ብየ ጽፌኣለሁ። ቅድስ ኣጎስጢኖስም ‘ኢየሱስ እኔ መንገድ እውነትና ሕይወት ብሎ መንገሩ የግድ ነበር፤ ምክንያቱም መንገዱን ኣንዴ ካወቅን ከዛ ባሻገር ወዳለው መድረስ የግድ ስለሆነ፤ ይህ ከመንገድ ባሻገር ያለው እግዚአብሔር ኣብ ነው፤ ለክርስትያኖች እንዲሁም ለእያንዳንዳችን ወደ እግዚአብሔር ኣብ ለመድረስ በኢየሱስ መመራት ኣለብን፤ እውነት በሆነው ቃሉ በመመራት የሕይወት ስጦታን እንቀበል። ‘ዓይኖችህን ክፈት መንፈሳዊ ጆሮችህን ለማዳመጥ ዝግጁ ኣድርጋቸው ከንፈሮችህን ክፈት ልብህን ዝግጁ ኣድርገው እንዲህ በማድረግህ በፍጡራን ሁሉ እግዚአብሔርን ለማየት ለመስማት ለማክበር ለማፍቀር ምስጋና ለማቅረብ ትችላለህ’ የሚለውን የቅዱስ ቦናቨንቱራ ጥሪ የእኛ እናድረገው።

የተከበራችሁ፤ መንገድ እውነትና ሕይወት የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የመስበክ ኃልፊነት የቤተ ክርስትያን ዋነኛ ተል እኮ ነው። የጌታ እረኞችና በሁሉም የቤተ ክርስትያን ተልእኮ የሚገኙ ይህንን ኣስደሳች የደኅንነት ዜና ለሁሉም እንዲያዳርሱ ዘወትር እንድትረዳቸው እመቤታችን ድንግል ማርያምን እንለምናት።

ከንግሥተ ሰማያት ጸሎት በኋላ፤

ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ ትናንትና በሊዝቦና በተፈጸመው የእመምኔት ኪያራ ዘኢየሱስ ሕፃን ሥርዓተ ብፅዕና የፖርቱጋል ቤተ ክርስትያን ደስታ ተካፋይ ነኝ፤ እንዲሁም ዛሬ ዕለት በሳልቫዶር ባህያ በሚፈጸመው የእናቴ ዱልሰ ሎፐስ ፖንተስ ሥርዓተ ብፅዕና የብራዚል ቤተ ክርስትያን ደስታ ተካፋይ ነኝ። ሁለቱም ሴቶች በንጽሕት ድንግል ማርያም ጥበቃ ሥር የተመሠረቱ ገዳማት ኣባላት ናቸው። ምስጋና ለጌታና ለእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ይሁን።








All the contents on this site are copyrighted ©.