2011-05-23 13:23:56

የመካከለኛው ምሥራቅ ማኅበረ ክርስያን ወቅታዊ ሁኔታ


በቅድስት መሬት የፍራንቸስካውያን ማኅበር ቅዱሳት ሥፍራ እና ንብረት ጠባቂ ግብጻዊ የማኅበሩ አባል አባ ኢብራሂም ፋልታስ በዓረብ ክልል አገሮች በጠቅላላ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚኖረው ማኅበረ ክርስትያን በማስመልከት RealAudioMP3 ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በኢራቅ፣ በቅድስት መሬት በፍስልጥኤም እና በእስራኤል መካከል ያለው ግጭት በጠቅላላ በዓረብ አገሮች ያለው ማኅበረ ክርስትያን ለአክራሪያንእ እና ጸንፈኞች ሙስሊሞች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ኢላማ በመሆናቸውም ምክንያት፣ ለተለያየ አደጋ ተጋልጠው እንደሚገኙ በቅርቡ በግብጽ እየታየ ያለው ጸረ ክርስትያን አመጽ መሠረት በማድረግ ካብራሩ በኋላ፣ የክልሉ ማኅበረ ክርስትያን ከዚህ ችግር ለመላቀቅ እምነቱን በነጻነት እና በሰላም ለመኖር ብቻ ሳይሆን የገዛ እራሱን ሕይወት ከሞት አደጋ ለማላቀቅ ለመሰደድ መገደዱ ጠቅሰው፣ እ.ኤ.አ. በ 2005 ዓ.ም. ዳግማዊው ኢንቲፋድ ከተቀጣጠለበት ዓመት ወዲህ የክርስትያኖች መሰደድ ገታ ያለ ቢመስልም፣ እስራኤል እና ፍልስጥኤም የክልሉን ችግር ለመፍታት የሚቻለው በውይይት መድረክ ብቻ መሆኑ ተገንዝበው አመጽ እና ግብረ መልስ ሰላም እንዲርቅ ያደርጋል፣ ምክንያቱን በበላይነት ኃይል የሚጸና ሰላም እና ሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ እንደሌለ የተረጋገጠ ነው። ስለዚህ ይኸንን ተገንዝበው አወዛጋቢው ናቸው የሚባሉት ሰላም የሚነሱ ጥያቄዎቻቸውን በውይይት መድረክ ለመፍታት ቆራጥ ውሳኔ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ፍራንቸስካውያን የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘ አሲዚ መንፈሳዊነት በመከተል የግጭቱ ተወናያን የሆኑትን ሁሉ ወደ ውይይት መድረክ እንዲመለሱ ካለ መታከት በተለያየ መልኩ ከማስገንዘብ እና ጥሪ ከማቅረብ አለ መቆጠባቸው አባ ፋልታስ በማብራራት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.