2011-05-23 13:24:48

የመከላከያ ኃይል አባላት 53ኛው ዓለም አቀፍ መንፈሳዊ ንግደት በሉርድ


ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ የመከላከያ ኃይል አባላት በየዓመቱ በሉርድ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ የሚያከናውኑት መንፈሳዊ ንግደት መሠረት ዘንድሮ “በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ” በሚል መንፈሳዊ ርእሰ ጉዳይ የተመራው 53ኛውን RealAudioMP3 ዓለም አቀፍ መንፈሳዊ ንግደት በአንድ አባት ሥር ያለው አንድነት እና ኅብረት አባታችን ሆይ በሚለው ጸሎት የሚረጋገጠውን እውነት መርህ በማድረግ 3 ሺሕ 5 መቶ ከኢጣሊያ የመከላከያ ሃይል አባላት የተወጣጡ በተለያየ ሰላም በማስከበር ተልእኮ የወደቁት የ 13 የኢጣሊያ የመከላከያ ኃይል አባላት ቤተሰብ ያሳተፈ እንደሚሆን ነጋዲያኑን የሚመሩት የኢጣሊያ የመከላከያ ኃይል አባላት መንፍሳዊ ጉዳይ የሚከታተለው ተልእኮ ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ቪቸንዞ ፐልቪ እዳመለከቱ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

የመከላከያ ኃይል አባላት የሰላም ልኡካን እንዲሆኑ የተጠሩ ናቸው፣ ስለዚህ ጦርነት ለማስወገድ እና ሰላም በመገንባት ተልእኮ አቢይ ኃላፊነት እንዳላቸው ብፁዕ አቡነ ፐልቪ ስለ ሚካሄደው መንፈሳዊ ንግደት በማስደገፍ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው። ውይይት መቀራረብ መከባበር የሰፈነበት ዓለም ለማነጽ በሚደረገው ተልእኮ የመከላከያ ኃይል አባላት ኃላፊነት አቢይ ሚና ያለው መሆኑ አበክረው፣ ስለዚህ ወታደር ወይም የመከላከያ ኃይል አባል ሲባል የሕይወት ባህል ለማስፋፋት የሚዋጋ እንጂ የሞት ባህል የሚያስፋፋ ማለት እንዳልሆነ በማብራራት፣ የመከላከያ ሃይል ባህርይ ጸረ መገነጣጠል እና ጸረ ጦርነት ነው። ስለዚህ ጸረ የሞት ባህል የሚዋጋ የሰላም ኃይል ነው። ይኸንን መሠረታዊው ባህርዩ ተገንዝቦ እንዲከተለው በማርያም ጥበቃ እና አማላጅነት አማካኝነት ወደ ሁሉም አባት ወደ ሆነው እግዚአብሄር በኅብረት ጸሎት የሚያሳርጉበት የተቀደሰ ወቅት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.