2011-05-23 13:22:52

ብራዚል፦ የእናቴ የእግዚአብሔር አገልጋይ ዱልሰ ሎፐስ ፖንተስ የብፅዕና አዋጅ


የብራዚል እናቴ ተረዛ በሚል ልዩ መጠሪያ በሕዝብ የሚታወቅቱ እናቴ የእግዚአብሔር አገልጋይ ዱልሰ ሎፐስ ፖንተስ በብራዚል ዘ ባሂያ ትላትና በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ቅዱስ አባታችንን ወክለው የሳን ፓውሎ ዲ ባሂያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ጀራርልዶ ማጀላ አንጀሎ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ብፅዕና እንደታወጀላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

እናቴ ብፅእት ተረዛ ዘ ብራዚል (እናቴ ዲልሰ ሎፐስስ ፖንተስ) በብራዚል ሳልቫዶር ዲ ባሂያ RealAudioMP3 እ.ኤ.አ በ 1914 ዓ.ም. ተወልደው እ.ኤ.አ በ 1992 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ለብፅዕና ብቁ የሚያሰኛቸው የብፅዕና እና የቅድስና ጉዳይ በሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር በኵል በሚደረገው ጥልቅ ጥናት መሠረት የሚቀርበው የክርስትያናዊ እና መንፈሳዊ ኃይሎች ውሳኔ የእኚህ የቤተ ክርስትያን ልጅ እናቴ የእግዚአብሔር አገልጋይ ዱልሰ ሎፐስ ፖንተስ ክርስትያናዊ እና መንፈሳዊ ባህርየ ነፍስ ወይንም ምግባረ ጻድቅ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. በይፋ እውቅና ተሰጥቶት በእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን በይፋ መታወጁ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።

የብፅዕና እና የቅድስና ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ በሰጡት መግለጫ፣ እናቴ የእግዚአብሔር አገልጋይ ዱልሰ በፍራንቸስካውያን ሶስተኛው የደናግል ማኅበር ተመካሪ ሆነው በመማር ላይ እያሉ በንጽሕት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር እናት የደናግል ልኡካን ማኅበር አባል በመሆን በዚሁ ማኅበር ገና በ 20 ዓመት እድሜያቸው የመጀምሪያ ማኅላ ፈጽመው ድኾንች በተለይ ደግሞ በተለያየ ችግር ምክንያት ከማኅበረሰብ ተነጥለው ባዘነ እና ተስፋ በቆረጠ ሕይወት የሚኖሩትን በመደገፍ እና ሰብአዊ መብታቸው እና ፍቃድ ተከብሮላቸው ከሚኖሩበት ኅብረተሰብ ጋር ተቀላቅለው ለመኖር የሚያበቃቸው መንፈሳዊ ሰብአዊ ሕንጸት በማቅረብ ሲያገለግሉ፣ እ.ኤ.አ. በ 1939 ዓ.ም. በጉልበት ሥራ የሚተዳደሩት የተናቁት በድኽነት የሚኖሩት ቤተሰብ ልጆች ተገቢ ሕንጸት የሚያገኙበት የቅዱስ አንጦኒዮስ ተቋም መሥረተው ቀጥለውም ድኾች ተገቢ የሕክምና አገልግሎት የሚያገኙበት አብይ የሕክምና አገልግሎት መስጫ ጣቢያ በማቋቋም ይኽ አይነቱ አገልግሎታቸውም የድኾች እናት የሚል መጠሪያ እንዳሰጣቸው ለማወቅ ተችለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በተለያየ ወቅት በብራዚል ሐዋርያዊ እና ይፋዊ ጉብኝት ባካሄዱበት ወቅት እና በሌላ መንፈሳዊ አጋጣሚዎችም ጭምር ከእኚህ የቤተ ክርስትያን ልጅ ጋር መገናኘታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ በእሳቸው መንፍሳዊነት የሚመራው በታላቅነቱ ቀዳሚ ሥፍራ ይዞ የሚገኘው ሰብአዊነት ማእከል ያደረገው እናቴ ዱልሰ ማኅበራዊ ተግባር በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የግብረ ሰናይ ማኅበር 2 ሺህ 3 መቶ ተባባሪ አባላት እና 600 የበጎ ፈቃድ አባላት ያቀፈ በብራዚል እና በተለያዩ አገሮች አገልግሎት የሚሰጠው ማኅበር እ.ኤ.አ. በ 1959 ዓ.ም. መቋቋሙም ከቅድስት መንበር የተላለፈው መግለጫ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.