2011-05-20 14:13:19

የስደተኛው የመተዳደሪያ ፖለቲካ የሰብአዊ መብት እና ፍቃድ የሚገታ እንዳይሆን


የስደተኞች እና የተጓዦች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ እና ዋና ጸሓፊያቸው አባ ጋብሪየለ ቤንቶሊዮ እ.ኤ.አ. ከግንቦት 2 ቀን እስከ ግንቦት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. በአውስትራሊያ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ በአውስትራሊያ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የስደተኞች እና RealAudioMP3 የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ድርገት ተጠሪዎች እና ከአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ጋር መገናኘታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ፣ በአውስትራሊያ ካለው 21 ሚሊዮን የሕዝብ ብዛት ውስጥ 5 ሚሊዮን በአውስትራሊያ የሚኖር የስደተኛው ሠራተኛ ብዛት ሲሆን፣ 22 ሺሕ 500 ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ ተፈናቃይ ስደተኞች እንዲሁም 2 ሺህ 350 የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኛ ብዛት ያካተተ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ቨሊያ ከሐዋርያዊ ጉብኝት መልስ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱ የሚዘክረ ነው።

በአውስትራሊያ ለስደተኛው እና ለተጓዡ የሚሰጠው ሐዋርያዊ አገልግሎት የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የስደተኛው እና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የሚሰጠው መሠረታዊ መመሪያ በመከተል፣ የአካባቢው ማህበራዊ ፖለቲካዊ እና ኤክኖሚያዊ ሁኔታ ግምት በመስጠት፣ ሆኖም የሰው ልጅ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ማእከል ያደረገ ከመሆኑም ባሻገር በበለጸገው ዓለም የሚታየው በቁጥር ከፍ ያለው በእድሜ የገፋው የአንዛውንት ብዛት ከቀን ወደ ቀን ከፍ እያለ የወሊድ ቁጥር ማነስ ያንሰራፋበት በመሆኑም ይኸንን ሁሉ በማመዛዘን በነዚህ አገሮች የስደተኛው ወጣት ብዛት እና በስደተኛው የወሊድ ቁጥር ከፍ ማለት አማካኝነት የሚስተካከል መሆኑን በማብራራት ስለዚህ ከስደተኛው የኅብረተሰብ ክፍል ውይይት የሚያበረታታ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ነው ብለዋል።

ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሁሉም በመግባባት በመከባበር በሰላም ለመኖር እንዲችል የሚደገፍ ሰብአዊ መንፈሳዊ ማኅበራዊ ሕንጸት አማካኝነት ስደተኛው የተስተናገደበት አገር ባህል እና ልምድ አውቆ እና በማክበር የራሱን ጭምር በማስተዋወቅ ካለ መነጣጠል ለመኖር የሚያግዝ የምታቀርበው ድጋፍ በሁሉም በስደተኛውም ይሁን በአገሪቱ መንግሥት እውቅና ያገኝ የተመሰገነም ነው ካሉ በኋላ፣ በአስትራሊያ የክህነት እና የገዳማዊ ሕይወት ጥሪ በአገሪቱ ዜጋ ብቻ የሚሸፈን ሳይሆን የተስተናገደው ስደተኛው የኅብረተሰብ ክፍል ጭምር የሚያጠቃልል ነው እንዳሉ ከሐዋርያዊው ጉብኝት መልስ ከራዲዮ ቫቲካን ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱ ለማወቅ ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.