2011-05-20 14:15:30

የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የመታሰቢያ ሐወልት


ከትላትና በስትያ ሮማ በሚገኘው ተርሚኒ በሚል መጠሪያ በሚታወቀው ብሔራዊ እና ዓለም አቀፍ የባቡር ጣቢያ ክልል ለሮማው ጳጳስ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መታሰቢያ የተሠራው አቢይ ሐወልት RealAudioMP3 ትላትና መመረቁ ሲገለጥ፣ የቆመው ሐወልት ለመመረቅ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት የማርያም የምስጋና ጸሎት የሚዚቃ ቅኝት እንዲሁም የተለያዩ አበይት የኢጣሊያ ሙዚቀኞች መሳተፋቸው ሲገለጥ፣ በኦሊቪየሮ ራኡናልዲ ሐወልት ቀራጭ እና የሥነ ቅብ ባለ ሙያ የቀረጸው የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ምስል የተቀረጸበት ሐወልት በመባረክ የመረቁት የሮማ ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ መሆናቸው ሲገለጥ፣ ሐወልቱ መታሰቢያ ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ወቅት ገዛ እራሱን እየለየ በተገለለ ሕይወት ለመኖር የተፈተነው ዓለም ከዚህ ችግር ተላቆ በመግባባት በመከባበር እና በመቀባበል እንዲኖር የሚያሳስብ ነው ሲሉ፣ የሮማ ከተማ ከንቲባ ጃኒ አለማኖ በበኩላቸውም የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ሐወልት በሮማ ተርሚኒ ክልል እንዲቆም መደረጉ በርግጥ ክልሉ ካለው እና ከሚሰጠው ዓለም አቀፋዊ እና ብሔርዊ አቀፍ አገልግሎት አንጻር ዘወትር እንዲዘከሩ እና የኖሩባት ከተማ በሳቸው አማላጅነት የእግዚአብሔር ጥበቃ እንዳይለያት የሚል ጸሎት ለማረጋገጥ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.