2011-05-20 14:14:18

የመላ ላቲን አሜሪካ እና ካሪቢያንን ብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጠቅላይ ጉባኤ


እ.ኤ.አ. ግንቦት 16 ቀን 2011 ዓ.ም. በኡራጉዋይ በሞንተቪደኦ ከተማ የላቲን አሜሪካ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ድርገት ሊቀ መንበር እና የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦለት በመሩት መሥታዕተ ቅዳሴ ተጀምሮ እ.ኤ.አ. ነገ ግንቦት 21 ቀን 2011 ዓ.ም. የሚፈጸመው RealAudioMP3 የመላ ላቲን አሜሪካ እና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት 33ኛው ጠቅላይ ስብሰባ ትላትና የዚሁ ጳጳሳዊ ምክር ቤት አዲስ ሊቀ መንበር እና የመስተዳድር አባላት ብፁዓን ጳጳሳት እንደመረጠ የላቲን አመሪካ እና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ያሰራጨው መግለጫ ይጠቁማል።

የዚህ የመላ ላቲን አመሪካ እና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አዲስ ሊቀ መንበር በሜክሲኮ የትላልነፓንትላ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ካሮሎስ አጉያር ረተስ፣ ምክትል ሊቀ መንበር በኮልምቢያ የበጎታ ሊቀ ጳጳስ የአገሪቱ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሩበን ሳላዛር ጎመዝ ሁለተኛ ምክትል ሊቀ መንበር እንዲሆኑ በብራዚል የካምፖ ግራንደ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲማስ ላራ ባርቦሳን መምረጡ ከመግለጫው ለመረዳት ሲቻል፣ አዲሱ የዚህ የመላ ላቲን አመሪካ እና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አጉይራ ረተስ በቅድሚያ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ለዚህ ኃላፊነት ሲመርጣቸው በሳቸው ላይ ያለው እምነት የሚመሰክር ተግባር መሆኑ ገልጠው፣ ተጋባእያን ብፁዓን ጳጳሳትን በማመስገን፣ ሆኖም በዚህ በተቀበሉት አዲስ ኃላፊነት የሁሉም ብፁዓን ጳጳሳት እና ውሉደ ክህነት ዓለማውያን ምእመናን ጸሎት እንዳይለያቸው አደራ ካሉ በኋላ፣ የላቲን አሜሪካ እና የካሪቢያን ብፁዓን ጳጳስት ምክር ቤት ከመንበረ ጴጥሮስ ጋር ያለው ጥብቅ ግኑኝነት እና በዚህ ሥልጣን ሥር የሚመራ መሆኑ በማስታወስ ከሌሎች አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጋር ጥብቅ ግኑኝነት እና መቀራረብ እንዳለው አስታውሰው፣ ባጠቃላይ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ኵላዊነት ባኅርይ መግለጫ ነው ሲሉ ምክትል ሊቀ መንበር እንዲሆኑ የተመረጡት ብፁዕ አቡነ ሩበን ሳላዛር ጎመዝ በበኵላቸውም በላቲን አሜሪካ እና ካሪቢያን እየተረጋገጠ ያለው ለውጥ እና ሂደት እግምት ውስጥ በማስገባት ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የእምነት የተስፋ እና የፍቅር ምልክት ብቻ ሳትሆን ሁሉም ሞቶ ሞትን አሸንፎ በተነሣው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለው እምነት በቃል እና በሕይወት እንዲመሰክር በዚህ እምነት እና ይኸንን እምነት መሠረት በሚያደርግ ሕንጸት አማካኝነት የሚያጋጥመው ዘርፈ ብዙ ተጋርጦ ለማስወገድ እንዲችል የምታንጽ ነች እንዳሉ ከመላ ላቲን አሜሪካ እና ካሪቢያን ጳጳሳዊ ምክር ቤት የተላለፈ መግለጫ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.