Home Archivio
2011-05-20 14:17:01
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በትውልድ አገራቸው ጀርመን
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በትውልድ አገራቸው ጀርመን እፊታችን መስከረም ወር 2011 ዓ.ም. ይፋዊ እና ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ በሚፈጽሙት መንፈሳዊ እና ባህላዊ መርሃ ግብሮች ለመሳተፍ የሚጠይቀው የምእመን
እና የሥነ ባህል ሊቃውንት ብዛት እጅግ ከፍ እያለ መምጣቱ ይኸንን ሐዋርያዊ ጉብኝት ማእከል በማድረግ ስለ ጉዳዩ የተለያዩ መግለጫዎች የሚሰራጭበት ድረ ገጽ በጠቅላላ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ 28 ሺህ ሕዝብ መመዝገቡ ሲር የዜና አገልግሎት ድረ ገጹ ጠቀስ ያሰራጨው የዜና ምንጭ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን በጀርመን ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ በርሊን እ.ኤ.አ መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ.ም. በሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ መስከረም 23 ቀን በሚመሩት ጸሎት ሰርክ፣ እንዲሁም መስከረም 24 በኤርፉርት በሚመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ በመጨረሻም መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ.ም. በፍሪበርግ በሚመሩት የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ለመሳተፍ የሚጠይቀው የምእመናን ብዛት ከቀን ወደ ቀን ከፍ እያለ መምጣቱ የጀርመን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሰጠው መግለጫ የጠቀሰ ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።
All the contents on this site are copyrighted ©.