2011-05-20 14:08:11

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ ወጣቱ ትውልድ ለሰላም እና ለፍትህ ማነጽ


እ.ኤ.አ. ሁሌ በአዲስ ዓመት መግቢያ ጥር 1 ቀን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ኵላዊ የሰላም መልእክት እንደሚያስተላልፉ የሚዘከር ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን 2012 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲቶስ 16ኛ የሚያስተላልፉት የሰላም መልእክት “ወጣቱ ትውልድ ለሰላም እና ለፍትህ ማነጽ” በሚል ርእስ ሥር የተመራ እንደሚሆን የፍትሕ እና የሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ትላትና ካሰራጨው መግለጫ RealAudioMP3 ለመረዳት ተችለዋል። ቅዱስነታቸው በዓለም እና በሕዝቦች መካከል አስቸኳይ እና አንገብጋቢ ጥያቄ የሆነው እርሱም የተፈጥሮ ሃብት በእኩል ለማዳረስ መሠረታዊው የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ዋስትና የሚሰጥ በሙላት እንዲኖር የሚያደርግ በሰላም እና ፍትህ ላይ የጸና የማኅበራዊ ሥርዓት እንዲረጋገጥ የሚለው ወጣቱን ትውልድ ማዳመጥ እና አቢይ ግምት መስጠት ወሳኝ መሆኑ በመግለጥ፣ በዓለማችን አንገብጋቢ እና ወቅታዊነት ያለው ጥያቄ የተገባ መሆኑ በማስታወስ፣ ስለዚህ አዲስ ወንድማማችነት መቀራረብ እና ሰላም ፍትህ የሰፈነበት ዓለም እውን ለማድረግ፣ ወጣቱ ትውልድ በነጻነት እና በኃላፊነት መንፈስ ገዛ እራሱን ለመግለጥ የሚያስችለው አዲስ ዓለም ለመገንባት መሠረት የሚጥለው ሁኔታ ሊመቻችለት የተገባ እና አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑ ቅዱስ አብታችን በሚያስተላልፉት መልእክት እንደሚያሰምሩበት የፍትህ እና የሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያሰራጨው መልእክት ያመለክታል። ቤተ ክርስትያን ወጣቱ ትውልድ የነገ ብሩህ ተስፋ መሆኑ በማመን በማስተናገድ እና በመቀበል “ሁሉን ነገር የሚለውጥ አዲስ የሚያደረግ” (ዮሓንስ ራዕይ ምዕ.21 ቁ. 5) የፍቅር ፍጹም አርአያ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቅረብ እንዲቀበሉትም እንደምታስተምር የሚያረጋገጥ መልእክት መሆኑ መግለጫው ይጠቁማል።
የሕዝባዊ ጉዳይ የሚያስተዳድሩ የመንግሥት የበላይ አካላት፣ የመንግሥት እና የአገልግሎት መሥጫ መዋቅሮች፣ የሚደነገጉ ሕጎች እና አካባቢም ጭምር ከነገር ባሻገር የሆነው የላቀው ወደ ላይ የሚያቀናው ሰብአዊነት የተካነው በማድረግ ለወጣቱ ትውልድ የሚበጅ የሥራ እድል የሚፈጥር የነገ ሕይወቱ በፍቅር በሰላም በወንድማማችነት መንፍስ የሚመራበት እውነት ነጻነት ፍቅር ፍትህ የሰፈነበት ሁኔታ የሚፈጥር መሆን እንዳለበት ቅዱስ አባታችን በሚያስተላልፉት የሰላም መልእክት ተመልክቶ እንደሚገኝ የፍትህ እና የሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት መግለጫ በማብራራት፣ ቅዱስ አባታችን ይኽንን ነቢያዊ አድማስ ያለው ርእስ በመምረጥ ለሰላም እና ለፍትህ የሚደረገው ሕንጸት ሊከተለው የሚገባው ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ያስተላለፉት የሥነ ሕንጸት ሥልት የሚከተል ሲሆን፣ በዚህ በተወሳሰበው እና ዓለማዊነት ትሥሥር በተረጋገጠበት የምንኖርበት ዓለም ወጣቱ ትውልድ የሰላም እና የፍትህ መሣሪያ ሆኖ እንዲገኝ የሁሉም በኃላፊነት የተቀመጡ አካላት ቁርጥ ፈቃድ መሆን እንዳለበት የሚያሳስብ መሆኑ የፍትህ እና የሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት መግለጫ ይጠቁማል።
የስደተኛው የመተዳደሪያ ፖለቲካ የሰብአዊ መብት እና ፍቃድ የሚገታ እንዳይሆን
የስደተኞች እና የተጓዦች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ እና ዋና ጸሓፊያቸው አባ ጋብሪየለ ቤንቶሊዮ እ.ኤ.አ. ከግንቦት 2 ቀን እስከ ግንቦት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. በአውስትራሊያ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ በአውስትራሊያ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የስደተኞች እና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ድርገት ተጠሪዎች እና ከአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ጋር መገናኘታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ፣ በአውስትራሊያ ካለው 21 ሚሊዮን የሕዝብ ብዛት ውስጥ 5 ሚሊዮን በአውስትራሊያ የሚኖር የስደተኛው ሠራተኛ ብዛት ሲሆን፣ 22 ሺሕ 500 ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ ተፈናቃይ ስደተኞች እንዲሁም 2 ሺህ 350 የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኛ ብዛት ያካተተ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ቨሊያ ከሐዋርያዊ ጉብኝት መልስ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱ የሚዘክረ ነው።
በአውስትራሊያ ለስደተኛው እና ለተጓዡ የሚሰጠው ሐዋርያዊ አገልግሎት የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የስደተኛው እና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የሚሰጠው መሠረታዊ መመሪያ በመከተል፣ የአካባቢው ማህበራዊ ፖለቲካዊ እና ኤክኖሚያዊ ሁኔታ ግምት በመስጠት፣ ሆኖም የሰው ልጅ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ማእከል ያደረገ ከመሆኑም ባሻገር በበለጸገው ዓለም የሚታየው በቁጥር ከፍ ያለው በእድሜ የገፋው የአንዛውንት ብዛት ከቀን ወደ ቀን ከፍ እያለ የወሊድ ቁጥር ማነስ ያንሰራፋበት በመሆኑም ይኸንን ሁሉ በማመዛዘን በነዚህ አገሮች የስደተኛው ወጣት ብዛት እና በስደተኛው የወሊድ ቁጥር ከፍ ማለት አማካኝነት የሚስተካከል መሆኑን በማብራራት ስለዚህ ከስደተኛው የኅብረተሰብ ክፍል ውይይት የሚያበረታታ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ነው ብለዋል።
ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሁሉም በመግባባት በመከባበር በሰላም ለመኖር እንዲችል የሚደገፍ ሰብአዊ መንፈሳዊ ማኅበራዊ ሕንጸት አማካኝነት ስደተኛው የተስተናገደበት አገር ባህል እና ልምድ አውቆ እና በማክበር የራሱን ጭምር በማስተዋወቅ ካለ መነጣጠል ለመኖር የሚያግዝ የምታቀርበው ድጋፍ በሁሉም በስደተኛውም ይሁን በአገሪቱ መንግሥት እውቅና ያገኝ የተመሰገነም ነው ካሉ በኋላ፣ በአስትራሊያ የክህነት እና የገዳማዊ ሕይወት ጥሪ በአገሪቱ ዜጋ ብቻ የሚሸፈን ሳይሆን የተስተናገደው ስደተኛው የኅብረተሰብ ክፍል ጭምር የሚያጠቃልል ነው እንዳሉ ከሐዋርያዊው ጉብኝት መልስ ከራዲዮ ቫቲካን ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱ ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.