2011-05-18 15:03:36

የካቶሊክ እና የአግሊካን አቢያተ ክርስትያን የጋራ ውይይት


የካቶሊክ እና የአንግሊካን አቢያተ ክርስትያን ዓለም አቀፍ የጋራው ድርገት ሶስተኛው ዓለም አቀፍ ስብሰባው በኢጣሊያ በቢየላ አውራጃ በምትገኘው ቦዜ ከተማ በሚገኘው የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን መናንያን በሚያቅፈው በቦዜ ገዳም ከትላንትና ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑ ሲገለጥ፣ ይህ ስብሰባ እንደሚካሄድ ቀደም ተብሎ የዛሬ አንድ ዓመት ከስድስት ወር RealAudioMP3 በፊት በቫቲካን በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እና የመላ አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳስ ሮዋን ዊሊያምስ መካከል በተካሄደው ግኑኝነት ቀድሞ መወሰኑ የሚዘከር ሲሆን፣ የዚህ ትላትና የተጀመረው የካቶሊክ እና የአንግሊካን አቢያተ ክርስያን የጋራው ውይይት ርእሰ ጉዳይ ውህደት የሚል ሆኖ፣ ይህ የክርስትያኖች አንድነት በሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ድጋፍ ጭምር የሚካሄድ መሆኑም ለማወቅ ሲቻል፣ በጋራው ውይይት የሚሳተፉት የክርስትያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የልኡካን አባላት ብፁዕ አቡነ ማርክ ላንጋም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የዚህ በመካሄድ ላይ ያለው ስብሰባ ርእሰ ጉዳይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከካንተርበርይ ሊቅ ጳጳስ ሮዋን ዊሊያም ጋር በቫቲካን ባካሄዱት የጋራው ግኑኝነት ወቅት ያቀረቡት ሐሳብ እንደነበርም ሲታወስ፣ የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን ልዩነት ሥረ ነገሩ በትክክል ለመለየት ሁለቱ አቢያተ ክርስትያብ አንድ የሚያደርጋቸው የጋራ አካፋይ የሆነው ሥርወ እምነት አቢይ ግምት ለመስጠት የሚል ውሳኔ ላይ ያተኮረ የሚለያየውን በትክክል አጢኖ ተገቢ መልስ በመስጠት ወደ አንድነት ለማቅናት የሚደግፍ ስብሰባ መሆኑ ገልጠዋል።

የአቢያተ ክርስትያን ውህደት እንዲረጋገጥ የሚደረገው የጋራው ውይይት የእግዚአብሔር ፍቃድ በጋራ ለይቶ ለማወቅ የሚያግዝ እና ይኸንን ፈቃድ መሠረት ያደረገ ውህደት እንዲረጋገጥ የሚደግፍ ጭምር ነው። ስለዚህ የጋራው ውይይት ለገዛ እራሱ ጸሎት መሆኑ አብራርተው፣ የአቢያተ ክርስትያን ውህደት የወንጌል ታማኝነት አቢይ ድጋፍ እና የሚሰጠው ወንጌላዊ ምስክርነት አሳማኝነቱ የላቀ እንደሚያደረገው አያጠራጥርም፣ ስለዚህ የጋራው ስብሰባ የአቢያተ ክርስትያን አንድነት ለሚቀርበው ወንጌላዊ ምስክርነት ኃይል መሆኑ የሚመሰክር ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.