2011-05-18 15:00:14

የኩላዊት ቤተ ክርስትያን የማህበራዊ ጉዳይ ሥርወ ትምህርት


የፍትሕ እና የሰላም ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያዘጋጀው ፍትሕ እና ዓለማዊነት ትስስር፣ ቤተ ክርስትያን የፍቅር እና የእውነት እናት እና መምህር በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. ግንቦት 16 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ የተጀመረው ዓውደ ጥናት እ.ኤ.አ. ዛሬ ግንቦት 18 ቀን 2011 ዓ.ም. መጠናቀቁ የቅድስት RealAudioMP3 መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ረሩም ኖቫሩም - አዳዲስ ነገሮች በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. በ 1891 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ሊዮነ 13ኛ የወዝአደሩ /የላብአደሩ/ የጉልበት ሠራተኛው ጥያቄዎች ላይ በማነጣጠር ቤተ ክርስትያን ለዚህ ዓቢይ ጥያቄ የምትሰጠው የማኅበራዊ ሥርወ መመሪያ እና ትምህርት የሚያብራራ የደረሱት ዓዋዲ መልእክት መሠረት በማድረግ፣ እ.ኤ.አ. 1961 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ ማተር ኤት ማጂስትራ - እናት እና መምህር በሚል ርእስ ሥር፣ ቤተ ክርስትያን ለማኅበራዊ ጥያቄዎች የምትሰጠውን መልስ አዘል ዓዋዲ መልእክት መሠረት በጠቅላላ ከባለፈው ዘመን ጀምሮ እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ካሪታስ ኢን ቨሪታተ - ፍቅር በሐቅ በተሰኘው የሰው ልጅ የተሟላ እና የተወሃደ እድገት ላይ ያተኮረ የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ ሥርወ እምነት የሚያመለክተው የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ያጠቃለለ መላ የቤተ ክርስያን የማኅበራዊ ሥርወ ትምህርት ሂደት መለስ ብሎ የሚቃኝ እና ቀጣይነቱን የሚያበክር ዓውደ ጥናት መሆኑ ሲገለጥ፣ ይህ ጳጳሳዊ የፍትሕ እና የሰላም ምክር ቤት ያዘጋጀው ዓዋደ ጥናት በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ 23ኛ እ.ኤ.አ. በ 1961 ዓ.ም. እናት እና መምህር የበሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት 50ኛው ዓመት ለመዘከር ብቻ ሳይሆን፣ የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጥያቄዎች መልስ ላይ በማተኮር ከባለፈው ዘመን ጀምሮ ሂደቱ እና እድገቱ በመዳሰስ በወቅቱ በተለይ ደግሞ በዚህ ዓለማዊ ትሥሥር በተረጋገጠበት ዘመን ለሚቀርቡት አዳዲስ የማኅበራዊ ነክ ጥያቄዎች የቤተ ክርስትያን ሥርወ ትምህርት የሚሰጠው መልስ ላይ ጠንቅቆ ለመገንዘብ የተወያየ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።

የፍትህ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኮድዎ አፒያ ቱርኩሶን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ ሥርወ እምነት እና ለአዳዲስ የማኅበራዊ ጉዳይ ጥያቄዎች ተጋርጦ ተገቢ መልስ ለመስጠት ዓለማዊ ምእመን የቤተ ክርስትያን ትምህርት መሠረት ጥረት በማድረግ ሂደት ተቀዳሚው ሚና እንደሚጫወት ገልጠው፣ ዓለማችን በተለያዩ ዘርፎች በሥነ ምርምር በእደ ጥበብ እድገት መሠረት ተፈጥሮን ቦታ እና ጊዜን ለመቆጣጠር ያደረገው እና እያከናወነው ያለው ጥረት፣ በእድገት ጎዳና ላይ የሚገኙት አገሮች ልኡላዊነታቸው በማወጅ በዓለማችን ይረጋገጥ የነበረው እና አዳዲስ ለውጦችን በመተንተን ቤተ ክርስትያን የምትሰጠው መመሪያ የዛሬ 50 ዓመት በፊት ቤተ ክርስትያን እናት እና መምህር በሚል ርእስ ሥር ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ 23ኛ በደረሱት ዓዋዲ ላይ ያሠፈሩት በዚያኑ ወቅት ሳይታጠር ነቢያዊ ገጽታ ያለው ጭምር መሆኑ ገልጠው፣ ዓለማችን እና በጠቅላላ የተፈጥሮ ሃብት የፖለቲካው መድረክ የማኅበራዊ ጥያቄዎች ጭምር ፍትህ መሠረት ባደረገ ሂደት መተዳደር እንዳለበት የሚያስተምር ነው ሲሉ፣ የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ፕሮፈሰር ፍላሚኒያ ጆቫነሊ በበኩላቸው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ዜጎች በተለይ ደግሞ ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል ለማኅበራዊ ነክ ጥያቄዎች ንቁ እና አስተዋይ እንዲሆን በዚሁ ጉዳይ እንዲታነጽ በማድረግ ዓለማችን ፍትሕ እና ሰላም የተረጋገጠበት ለማድረግ በማቀድ ቤተ ክርስትያን ለወጣት የኅብረትሰብ ክፍል የተሟል ሕንጸት በማቅረቡ ረገድ አቢይ ሚና እየተጫወተች ነው። ስለዚህ ይህ ዛሬ የተጠናቀቀው ዓወደ ጥናት የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ ሥርወ እምነት በቤተ ክርስትያን እቅዶች ዘንድ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካው በኤክኖሚው እና በማህበራዊ ዘርፍ ጭምር እግብር ላይ መዋል የሚችል ነው። ስለዚህ ለቤተ ክርስትይን ብቻ ሳይሆን ለዓለማችን ጠቃሚ እና ወሳኝም ነው ብለዋል።

ቤተ ክርስትያን በዓለም የሚነሱት ማኅበራዊ ፖለቲካዊ ኤክኖሚያዊ ጥያቄዎች በማዳመጥ ቀዳሚው ሥፍራ በመያዝ ዓለማውያን ምእመናንን በማሳተፍ በሥርወ እምነት እንዲሁም በሥልጣናዊ ትምህርትዋ በኩል መልስ ለመስጠት ተጠርታለች በማለት ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድተኛ ያሉትን ሐሳብ አስታውሰው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ከትላትና በስትያ በዚህ ዓወደ ጥናት የተሳተፉትን ተቀብለው መሪ ቃል ሲሰጡ፣ በዓለማችን እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. የተከሰተው የኤኮኖሚ ቀውስ እያስከተለው ያለው ማኅበራዊ ኤክኖሚያዊ ችግር በመጥቀስ ትርፍ ሳይሆን ሰው በእግዚአብሔር አምሳያ እና አርአያ በመፈጠሩ ምክንያት ላይ የጸናው ሰብአዊ መብቱ እና ፈቃድ በሁሉም መስክ ማእከል መሆን እንዳለበት ማሳሰባቸው ጠቀሰው የተካሄደው ዓውደ ጥናት ይኸንን በጥልቀት አስምሮበታል በማለት ሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.