2011-05-18 17:19:50

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮ (18.05.2011)


ኦሪት ዘፍጥረት 18፡20~23 ‘እንግዲህስ ወደ እኔ እንደ መጣች እንደ ጩኸትዋ አድርገው እንደ ሆነ ወርጄ አያለሁ፤ እንዲሁም ባይሆን አውቃለሁ። ሰዎቹም ከዚያ ፊታቸውን አቀኑ፥ ወደ ሰዶምም ሄዱ፤ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር። አብርሃምም ቀረበ አለም። በውኑ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ታጠፋለህን?’

ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ በክርትያን ጸሎት የጀመርነውን ትምህርተ ክርስትና በመቀጠል ዛሬ ሥጋ በሆነው ቃል፡ በጌታችን መድኃኒታችህ ኢየሱስ ክርስቶስ የተደመደመው በእግዚአብሔርና በሰው ልጅ መሀከል ስለነበረው ውይይት በታሪክ ውስጥ እንዴት እደነበር እንመለከታለን፤ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሮማውያን በጻፈው መል እክት የኣመንያን ኣባት በማለት በሚጠራው ኣብርሃም ጸሎት እንጀምራለን፤ ሲነበብ በሰማነው ቃለ እግዚአብሔር ኦሪት ዘፍጥረት 18 ላይ ኣብራሃም ኃጢኣተኛዋን የሰዶም ከተማ እግዚአብሔር እንዳይደመስሳት ሲያማልድ ሰምተናል። የኣብርሃም ጸሎት በምሕረትና በዕርቅ መጥፎውን ወደ መልካም ነገር ሊለውጥ በሚችል በእግዚአብሔር ፍትሓዊ ፍርድ ወይም ጽድቅ ላይ በሚወሰነው ፍትሕ ላይ ንጹሓን ከኃጢኣተኛ ጋር እንዳይደመስስ በሚያሳርገው ጸሎት እንመለከታለን። እግዚአብሔር የኃጢኣተኛ ሞት ሳይሆን የኃጢአተኛ ንስሓና ከሓጢአት ነጻ መውጣትን ይሻል። እግዚአብሔር የኣብራሃምን ጸሎት ሲመልስ ፍላጎቱ ኣብርሃም ባሰባቸው ኣምሳ ጻድቃን ሳይሆን ቢያንስ ኣሥር ወይም ኣምስ ጻድቃን የተገኙ እንደሆነ ሰዶምን ካቀደው የጥፋት መቅሰፍት ሊያድናት እንደሚፈልግ ይገልጻል። ከዚህ ፍጻሜ ብዙ ዓመታት በኋላ እግዚአብሔር በኤርምያስ ነቢይ ኣድርጎ ‘በኢየሩሳሌም መንገድ እየተመላለሳችሁ ሩጡ፥ ተመልከቱም፥ እወቁም፥ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ ፍርድን የሚያደርገውን እውነትንም የሚሻውን ሰው ታገኙ እንደሆነ ይቅር እላታለሁ።’ በማለት ኣንድ ሰው እንኳ ጻድቅ የተገኘ እንደሆነ ይቅር እንደሚላት ይገልጻል። በመጨርሻም እግዚኣብሔር ራሱ በመሆን በምሥጢረ ሥጋዌ ያኛው ኣንድ ንጹሕ ሰው ይሆናል። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ ስለሰው ልጅ ያሳረገው ለዓለም ሁሉ ደህንነትን ኣመጣ። በእርሱ ኣማካኝነት እንዲሁም በማይለወጠው መሓሪው የእግዚአብሔር ፍቅር ጸሎታችን ሳይሰማና መልስ ሳያገኝ እንደማይቀር በማመን እንጸልይ።








All the contents on this site are copyrighted ©.