2011-05-18 15:01:52

ኡራጉዋይ፣ የመላ ላቲን አሜሪካ እና ካሪቢያንን ብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ተቅላይ ጉባኤ


የመላ ላቲን አሜሪካ እና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. እስከ ግንቦት 21 ቀን 2011 ዓ.ም. የሚዘልቀው 33ኛው ጠቅላይ ስብሰባውን እ.ኤ.አ. ግንቦት 16 ቀን 2011 ዓ.ም. በኡራጉዋይ በሞንተቪደኦ ከተማ የላቲን አሜሪካ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ድርገት ሊቀ መንበር እና የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር RealAudioMP3 ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦለት በመሩት መሥታዕተ ቅዳሴ መጀመሩ ሲገለጥ፣ ይህ በመካሄድ ላይ ያለው ጉባኤ በመላ ላቲን አመሪካ እና በካሪቢያን እውነተኛ ለውጥ እና ኅዳሴ እንዲኖር የሚያደረግ ተብሎ የተነገረለት የፖለቲካው ርእዮተ ዓለም ውድቅ መሆኑ የክፍለ ዓለሙ ሕዝብ እና መንግሥታት ጠንቅቀው የሚያውቁት እውነት፣ ታሪክ ያረጋገጠው ገጠመኝ መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ኦለት ከቅዳሴው በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በማብራራት፣ በላቲን አሜሪካ የምእመናን ቁጥር እየቀነሰ ያለ ቢመስልም ቅሉ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እውነት በቁጥር ብዛት እና ማነስ እውነትነቱ የሚለካ እንዳልሆነ ገልጠው፣ እ.ኤ.አ. በ 2007 ዓ.ም. በብራዚል አፓረሲዳ ተካሂዶ የነበረው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የተሳተፉበት ሐዋርያዊ ተልእኮ ላይ በማነጣጠር በዚህ የቤተ ክርስትያን ተልእኮ የዓለማዊው ምእመን ተሳትፎ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ የሚመለከት የተሰጠው መመሪያ አቢይ ውጤት እያስጨበጠ ነው ብለዋል።

ብፁዕነታቸው በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃል ምልልስ በቅድሚያ በላቲን አመሪካ እና ካሪያቢያ ብፁዓን ጳጳሳት መካከል ያለው ኅብረት ከመንበረ ጴጥሮስ ጋር ላለው ኅብረት ምስክር ከመሆኑም ባሻገር የክልሉ ማኅበረ ክርስያን እንዳይደናገር በእምነት የሚያጸና ጸጋ ነው ብለዋል።

ይህ በመካሄድ ላይ ያለው የላቲን አመሪካ እና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጠቅላይ ጉባኤ ከ 2007 ዓ.ም. እስከ 2011 ዓ.ም የተገለገለበት የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እቅድ በመገምገም እስከ 2015 ዓ.ም. የሚገለገልበት የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እቅድ እንደሚወጥን እና የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር እና የመማክርት አባላት ምርጫ እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በዚህ በመካሄድ ላይ ባለው የመላ ላቲን አመሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጠቅላይ ጉባኤ ከተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ከካናዳ ከስፐይን ከፖርቱጋል ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የተወጣጡ ልኡካን ብፁዓን ጳጳሳት በኡራጉዋይ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ አንሰልሞ ፐኮራሪ ጭምር በመሳተፍ ላይ መሆናቸው የላቲን አመሪካ እና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ያሰራጨው የዜና ምንጭ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.