2011-05-16 16:56:53

የብፁዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ ስድስተኛ ዓመት የጳጳሳት በዓል

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ተከበረ 


በመላው ዓለም የሚከበረው ይህ በዓል በሀገራችን ለስድስተኛ ጊዜ በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተከብሮ ውሎዋል፡፡
ሚያዚያ 30, 2003 ዓ.ም በልደታ ማሪም ካቴድራል በተካሄደው በዓል ብፁዓን የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ ሃይማኖት አባቶች ገዳማውን ምዕመናን ተገኝተዋል፡፡

በዓሉን በማስመልከት በኢትዮጵያ የቅዱስ መንበር ባለሙሉ ስልጣን አንባሳደር ብፁዕ ሊቀጳጳሳ ጂ. ፓኒኩላም ምስጋና በማቅረብ በዓሉን በማስመልከት ቃለ ምዕዳን አድርገዋል፡፡

ብፁዕነታቸው ንግግራቸው በይበልጥ ያተኮረው በቅዱስ አባታችን ቤኔዲክቶስ 16 ኛ በቅድስት መንበር አገልጋዮች አገልጋይ ሆነው ከተሸሙ በኃላ ባሰተሙት ሁለት መጽሀፍት ላይ በመመርኮዝ ሰፋ ያለ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡

የመጀመሪው የዓለም ብርሀን በሚለው ርዕስ በቀረበው መፅሀፍ ሲሆን መጽሀፉ የሚያተኩረው በተለይ በዓለም መገናኛ ብዙሀን በቤተክርስቲያኒቱ በግልጽ የሚጠየቁትን በጋዜጠኛው ቪተር ሲዋልድ ጋር የተደረገው ቃለ መጠይቅ ላይ የተመረኮዘ ነው ጥያቄው ያተኮረው


ብፁዕነታቸው ለዚሁ በቂ መልስ መስጠታቸው ገልጸዋል፡፡


በመቀጠልም በሁለተኛ የመረጡት መፅሀፍ የናዝሬቱ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ከገባበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ትንሣኤ በሚለው ርዕሰ የቀረበው ፅሁፍ ትምህርት አቅርበዋል

ስለ መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ:-

ጥምቀት፣አስተምሮ ፣ፈውስ፣ትህትና፣ለወገኖች አንድነት መኖር ያደረጋቸው ፀሎት፣ የትህትና ሥራ ፣ የቅዱስ ቁርባን ራት ስጦታ፣ ኢፍትሀዊ ፍርድ ስቃይ፣ እንዲሁም ትንሳኤ በተመለከተ የቀረቡት የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን እተምህሮ ከዛሬ ዘመን የህይወት ተመክረቶ ጋር በማገናኘት ትምህርት ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ስድስተኛ ሲመተ ጵጵስና ግንቦት 2,2003 ዓ.ም. በመላው ዓለም በከፍተኛ መንፈሳዊ ስነስርዓት እነደሚከበር ተገልጽዋል፡፡
የብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የብፅዕና በዓል በመላው ኢትዮጵያ ተከበረ

 
ጥቅምት 22 ቀን በቅዱስ መንበር በታወጀው በዚሁ የብፅዕና በዓል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በመላው ሃገሪቱ በሚገኙ ሀገረስብከቶች በድምቀት አክብራ ውላለች፡፡

በዚሁ ዕለት በመላው ሀገረቱ በሚገኙ ካቴድራሎች በፁዓን ጳጳሳት የብፁዕ ዮሃሐንስ ዳግማዊ ምስል የያዘ ሥዕል በተዘጋጀለት የክብር ቦታ እንዲቀመጥ ሆኖዋል፡፡

በአዲስ አበባ ልደታ ለማርያም ካቴድራል የብፁዕ አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በተመራው ሥርዓተ ቅዳሴ የብፁዕ አባታችን የሕይወት ታሪካቸው ገድል በመዘርዘር በተለይ በክርስትና እምነት ላይ ያለ ፍረሃት መጓዝ እንዳለብን፣ ስለክርስቲያኖች አንድነት ተግተን መጸለይ ስለ ቤተሰብ ታላቅ የእግዚአብሔር መገለጫነት እንዲሁም ለወጣቶች ያላቸውን ፍቅር በመግለጽ በዘመናችን ታላቅ አባት እንደነበሩ ገልፀዋል፡፡



የብፁዕነታቸው በመጨረሻ የደረሰባቸው ስቃይ በመሸከም ሁሉ በስቀል በክርስቶስ መታለፍ እንደሚቻል ለዓለም በግልጥ በማሳየታቸው መስክረዋል፡፡



ብፁዕ ዳግማዊ ዮሐንስ ጳውሎስ በሞቱበት ዕለት ሕዝባዊ ብፅዕና ቢያገኙም ቤተክርስቲያን በአላት ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓት እስከዛሬ ድረስ ታላቅ አባት መሆናቸው ከመግለጽ ለብፅዕና ያበቃቸው ምክንያት በመግለጽ በይፋ ብፅዕነታቸው በሮም በቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ከአንድ ሚሊዮን በሚልጥ ሕዝብ ፊት በይፋ እንደሚታወጅ አሳውቀዋል፡፡



በዚሁም ምክንያት በቅዱሳን ሱታፌ የምናምን የክርስቶስ ወገኖች ሁሉ በእሳቸው አማላጅነት በመለመንና በመጠየቅ የምንሻውን ሁሉ እንድንለምን ቤተክርስቲያን ማሳወቁዋንና ለዚሁ ለእያንዳንዳችን በክርስትና ሕይወት ጠንክሮ መጓዝ ቃላቅ ተስፋ መሆኑን ገልጸዋል፡፡



በዓሉን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የብፁዕነታቸው መታወጅ የሚያሳይ ስርጭት ከቫቲካን ቅዱስ መንበር የሚደረገው መርሃ ግብር በቀጥታ በሳታላይት ቴክኒዮሎጂ በመጠቀም ምዕመናን እንዲከታተሉ ቁምስናው አድርጓል፡፡



ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በቅዱስ ጴጥሮስ መንበረ ሥልጣን በነበሩበት ጊዜያት በአገራችን ኢትዮጵያ ካርዲናል ፣ጳጳሳት፣ ሐዋርያ እና አስተዳዳሪ

በመሾም ታላቅ ተግባር የፈጸሙ ሲሆን በተለያየ ጊዜያት ወደ ቅዱስ መንበረ አንግድነት የሚመጡትን ኢትዮጵያዊ ምዕመናን በመቀበል አባታዊ ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡


እንዲሁም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የሃይማኖት አባቶችን በመቀበል በሁሉ አብያተክርስቲያን ስላለው ግንኙነት የጋራ አንድነት እንዲያገኝ ታላቅ ጥረት ያደረጉ አባት ነበሩ፡፡የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት
ማህበራዊና ህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ 








All the contents on this site are copyrighted ©.