2011-05-16 17:04:08

ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በተመለከተ የተላለፈ መልእክት


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

‹‹የወንዝ ፈሳሾች የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛሉ››(መዝ. 45፡4)

ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ

ግድብ ግንባታ በተመለከተ የተላለፈ መልእክት

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በልማት ዘርፍ በመሰለፍ ለዓመታት ለዜጎች ሁለንተናዊ ዕድገት የአቅሟን አሰተዋጽኦዎ ስታደርግ ቆይታለች አሁንም በተቀላጠፈ መልኩ በመንቀሳቀስ ላይ ናት፡፡ ድህነትን ለመቀነስ የምታደርገው ጥረት ይቀጥላል ይበረታታል ተግባራዊም እየሆነ ነው፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ የዓባይ ወንዝ ግድብ ግንባታን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በአንክሮት ስትከታተል ቆይታለች ፡፡ለሀገር ግንባታ የተዘረጋ ፕሮጀክት በመሆኑ በደስታና በጉጉት ተግባራዊነቱን እንጠባበቃለን፡፡ ለዓላማው ስኬታማነትም ከሕዝብ ጋር በመሆን ቤተክርስቲያናችን የምታደርገው ተሳትፎ ያስደስተናል፣ እግዚአብሔርም የሚወደው መንፈሳዊነትንም ያንፀባርቃል፡፡

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ሰሞኑን ባካሄድነው የጳጳሳት ጉባዔ ላይ ስለ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አጀንዳ ይዘን ተወያይተንበታል፡፡ በዚሁ ታላቅ የኢትዮጵያ ታሪክ ምዕራፍ ላይ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያልታከተ ተሳትፎ በጸሎትና በተግባር ለማድረግ ወስነናል፡፡

የውሳኔው ሙሉ ቃል

እኛ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጳጳሳት፡- የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ፣የአዲግራት ሀገረስብከት፣ የሀዋሳ ሀገረስብከት ፤የእምድብር ሀገረስብከት፣ የጋምቤላ ሀገረስብከት ፣የሆሳዕና ሀገረስብከት ፣የሐረር ሀገረ ስብከት፣ የመቂ ሀገረስብከት፣ የነቀምት ሀገረስብከት፣ የጂማ ቦንጋ ሀገረስብከት እና የሶዶ ሀገረስብከት፤ ለሀገራችን ለህዝባችን የልማት ግንባታ ይሆን ዘንድ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ የዓባይ ወንዝ ግድብ ፕሮጀክትን በተመለከተ ከቤተክርስቲያን ምዕመናን እና ሰራተኞች ጋር በመሆን ለኢትዮጵያ ዕድገትና ፍቅር የድርሻችንን ለመወጣት ከልብ ተነሳስተናል፡፡

ይህንን በጎ ዓላማ እና የኢኮኖሚ ግንባታ ዋልታና ማገር እንዲሆን የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን


አጠቃላይ አሀዙን በተመለከተ በቅርቡ ግልጽ ይደረጋል፡፡ ዕቅዱ ለሕዝቦች የልማት ግንባታ የጀርባ አጥንት በመሆኑ አምላካችን ይህንን በጎ ዓለማ ከግቡ ያደርስልን ዘንድ የዘወትር ጸሎታችን ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ዕድገት በጎ ዓላማ ካላቸው ጎን እንቆማለን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጳጳሳት

ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፌል

ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት እና የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ሮድሪጎ መሄያየሶዶ ሀገረስብከት ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ዩሐንስ ሚልዩራቲ የሐዋሳ ሀገረስብከት ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ወልደተንሳኤ ገ/ጊዩርጊስ የሀረርጌ ሀገረስብከት ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ቴዎድሮስ ቫንራይቨን የነቀምቴ ሀገረስብከት ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ተስፋሥላሴ መድzን የአዲግራት ሀገረስብከት ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ደስታ የመቂ ሀገረስብከት ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ሙሴ ገ/ጊዮርግስ የእምድብር ሀገረስብከት ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ገ/መድzን የጅማ ቦንጋ ሀገረስብከት ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ አንጀሎ ሞረስኪ የጋምቤላ ሀገረስብከት ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ወልደጊዮርጊስ ማቴዎስ የሆሳዕና ሀገረስብከት ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ልሳነክርስቶስ ማቴዎስ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ረዳት ጳጳስ

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት

ማህበራዊና ህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ








All the contents on this site are copyrighted ©.