2011-05-16 14:12:53

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ስደት እና መከራ ቢያጋጥማችሁም ወንጌልን ለማበሰር አትፍሩ


ከትላንትና በስትያ ጧት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከመቶ በላይ የሚገመቱት የጳጳሳዊ የተልእኮ ተግባር ጠቅላይ ጉባኤ ተሳታፊዎችን ተቀብለው ማነጋገራቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስነታቸው እነዚህ የአስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ በሚንከባከበው በቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፈርናንዶ ፊሎኒ ለተመሩት ተግባእያኑ በሰጡት መሪ ቃል፣ ዓለማችን ለተለያዩ አዳዲስ የባርነት ሥርዓት እና ችግሮች በተጋለጠበት በአሁኑ ወቅት፣ ስለ መጪው ሕይወት አለ መረጋገጥ በሥፋት ባንሰራፋበት የበለጸገ RealAudioMP3 ተብሎ የሚጠቀሰው ዓለም ሥነ ምግባርም ይሁን ግብረ ገብ ግምት የማይሰጥ ትርፍ ላይ ብቻ ባነጣጠረው የድኾች የስደተኞች በጭቆና የሚሰቃየው ተስፋው የጨለመበት የሕዝብ ብዛት ቁጥር ከፍ እንዲል የሚያደርገው ዓለማዊነት ትሥሥር እየተስፋፋ ባለበት ወቅት፣ ማኅበረ ክርስትያን የእውነተኛ ተስፋ ምስክር ሆኖ እንዲገኝ በማሳሰብ ክርስትያን የአስፍሆተ ወንጌል አባል ነው ብለዋል።

የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም ሰው ዘር እውነተኛ አዳኝ መሆኑ የሚያረጋገጥ የታመነ ወንጌላዊ ተልእኮ በዚህ አዳኝ ቃል ላይ ያለን ጽኑ እምነት በሕይወት የማይመሰከር ከሆነ ወንጌል በማበሠር የሚሰጠው ደስታ እና ክርስትያናዊ ተግባር ያለው ውበት ለመግለጥ ለሌላው ለማሳወቅ አንችልም፣ ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስትያን የእግዚአብሔር መንግሥት ለመገንባት በሚደረገው ተልእኮ ተሳታፊ መሆኑ ጠንቅቆ መገንዘብ አለበት። መላ ቤተ ክርስትያን በሁሉም የአገልግሎት ዘርፎችዋ የአስፍሆተ ወንጌል አግለግሎት ፈጻሚ ነች። የአገልግሎት ዘርፎችዋም ይሁን እያንዳንዱ የቤተ ክርስትያን አባል የዚህ የአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ ተሳታፊ ነው።

የአስፍሆተ ወንጌል ሚና ወደ ላይ የሚያቀናው መንፈሳዊው እና የሰው ልጅ እግዚአብሔርን መሻት ባህርይ ከነገር ባሻገር የሆነውን አድማስ እና የዚህ አድማስ ሙሉ መልስ የሆነው እግዚአብሔር በክርስቶስ አማካኝነት የገለጠው የማዳኑን እቅድ ወደ ጎን በማድረግ የማኅበራዊ እና የሰብአዊ ግብረ ሰናይ እቅድ አድርጎ ከመኖር ፈተና የምንላቀቀው በክርስቶስ እና በቃሉ ላይ በሙላት ስንጸና ብቻ ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ እና ቃል መመስከር በግልጽ ማወጅ አስፍፈላጊ ነው። አለ እውነተኛ እና ሕያው ምስክርነት፣ የእግዚአብሔር ቃል በገዛ እራሱ ታማኝ ቢሆንም ቅሉ፣ በቃል እና በሕይወት ካልተመሰከረ ለመረዳቱ የሚያዳግት የማያሳምን ሆኖ ይቀራል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ቤተ ክርስርትያን ምንም’ኳ በተልእኮዋ ምክንያት ስደት እና መከራ የሚጋፈጣት ቢሆንም ቅሉ ይኸንን የድኅነት ቃል፣ በቃል እና በሕይወት በማበሠር የክርስቶስ ብርሃን ወደ ዓለም ሁሉ ማድረስ ከሚለው ተልእኮዋ ወደ ኋላ አትልም፣ ወንጌል ማብሰር የህልውናዋ አመክንዮ ነው። ስለዚህ ክርስትያን ለስደተ እና መከራ የተጋለጠ ቢሆንም ቅሉ የዚህ ተልእኮ ተሳታፊ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.