2011-05-16 14:14:04

48ኛው ዓለም አቀፍ ስለ ጥሪ የጸሎት ቀን


የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትላትና እሁድ ስለ ጥሪ የሚጸለይበት 48ኛው ዓለም አቀፍ የጸሎት ቀን አክብራ መዋልዋ ሲገለጥ፣ ጥሪ የጸሎት ሐሳብ ሆኖ በሁሉም አቢያተ ክርስትያን ታስቦ ውሎአል። በሁሉም ሰበካዎች ስለ ጥሪ ጉዳይ የሚንከባከበው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በማነቃቃት በተልእኮ ወንጌል የሚሰማሩ በገዳማዊ እና በክህነት ጥሪ የሚኖሩ የአገልጋዮች ቁጥር ከፍ እንዲል ብቻ ሳይሆን፣ ወንጌላዊ ሕይወት በቃል እና በሕይወት የሚኖሩ ልኡካን፣ እግዚአብሔር ይሰጥ ዘንድ የሚጸለይበት ዓለም አቀፍ RealAudioMP3 ስለ ጥሪ የሚጸለይበት ቀን መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ጥሪ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ከሚመሠረተው የግል ግኑኝነት እና ከሚጸናው ጥልቅ እምነት የሚመነጭ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሚጠራው እግዚአብሔር ነው፣ ስለዚህ ጠሪው እግዚአብሔርን ለማዳመጥ ይቻል ዘንድ፣ ስለ ጥሪ ቤተሰብ ቁምስናዎች እና በጠቅላላ የማኅበረ ክርስትያን ጸሎት አስፈላጊ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን አንድ በአንድ በስም እየተጠራ ተከተለኝ ከማለቱ በፊት፣ የአባቱን ፍቃድ ለመለየት እና ይኸንን ፈቃድ ብቻ ለማገልገል በመሻት ለብቻው ገለል ብሎ በጸሎት መጠመዱ ቅዱስ አባታችን በማስታወስ፣ የተጠሩት እና የመረጣቸው ዕለት በዕለት በቃለ ሕይወት በመመገብ በመታነጽ በማዳን ተልእኮ እንዲሳተፉ አድርገዋል። ስለዚህ ተከተለኝ የሚለው የጌታችን ኢየሱስ ጥሪ፣ በማዳን እቅድ የሚያሳታፍ ጽናት እና ትጋት የሚጠይቅ ዕለት በዕለት የሚኖር መሆኑ ቅዱስ አባታችን ቀኑን ምክንያት በማድረግ ባስትላለፉት መልእክት በመግለጥ፣ ጥሪ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጓደኛ የሚያደርግ ከግላዊ ሕይወት እና ለራስ ብቻ ከሚለው የኑሮ ምርጫ እና ከግል ፍላጎት በመላቀቅ የእግዚአብሔር ፈቃድ በመኖር ወድማማችነት እና እርስ በእርስ መዋደድ የሚለው የደቀ መዛሙርት መለያ መሠረት የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ የማብሠር ኃላፊነት መልበስ ማለት ነው እንዳሉም የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

ኢየሱስን መከተል ትጋት እና ሕንጸት ጭምር ይጠይቃል፣ በተለይ ደግሞ በዚህ የእግዚአብሔር ድምጽ በሚያፍነው በተደናገረው ዓለም፣ በጽሞና ተከተለኝ የሚለው ቃሉን ለመለየት እና በጥልቅ ለማዳመጥ እና ገዛ እራስን ለእርሱ እና በእርሱ አማካኝነት ለወንድሞች አሳልፎ ለመስጠት እሺ እነሆኝ ለማለት መንፍሳዊ ሰብአዊ እና ባህላዊ ትጋት እና ሕንጸት እጅግ አስፈላጊ ነው። ስለዚህ ተከተለኝ የሚለውን ድምጹን የለዩ በዚህ የጥሪ መንገድ በመዘጋጀት ላይ የሚገኙት የማኅበረ ክርስትያን አባላትን በጸሎት መደገፍ የሁሉም ሰበካዎች እና ቁምስናዎች ኃላፊነት ነው። ለተጠራው እና ጥሪው ለተሰማው ጥሪው የግል ነው ተብሎ ለራሱ መተው የለበትም። በዚህ ጥሪ መሳተፍ እና የጥሪው ተካፋይ መሆን። እራስን አሳልፎ መስጠት ማንነትን የሚሰርዝ ሳይሆን የማንነት ትርጉም ሙላት ነው። ስለዚህ ወጣቱ የማኅበረ ክርስትያን አባል ጥሪውን ለመለየት እንዲችል ስለ ጥሪ ጉዳይ የሚመለከት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በሁሉም ሰበካዎች እና ቁምስናዎች ዘንድ አቢይ ትኵረት ሊሰጥበት ይግባል ካሉ በኋላ፣ ብፁዓን ጳጳሳት በቃል እና በሕይወት አብነት ሆነው በመምራት የተጠሩትን በመንከባከብ የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ በዓለም ሁሉ እንዲስተጋባ ካህናት ለዚህ ተልእኮ ማነቃቃት እና ማሰማራት፣ ካህን በቃል እና በሕይወት ክርስቶስን በማበሠር ከብፁዓን ጳጳሳት ጋር ኅብረት በማስቀደም በቤተ ክርስያን ትምህርት እና ሥልጣናዊ መሪነት ሥር የእግዚአብሔር ልጆችን እንዲመሩ የተጠሩ ናቸው ካሉ በኋላ፣ ሁሉም የማኅበረ ክርስትያን አባል እንደየ ኃላፍነቱ ለጥሪ መብዛት እንዲጸልይ ማሳሰባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.