2011-05-13 14:40:56

ፍትሕ እና ዓለማዊነት ትስስር፣ የፍቅር እና የእውነት እናት እና መምህር


የፍትሕ እና የሰላም ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያዘጋጀው ፍትሕ እና ዓለማዊነት ትስስር፣ ቤተ ክርስትያን የፍቅር እና የእውነት እናት እና መምህር በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. ከ ግንቦት 16 ቀን እስከ ግንቦት 18 ቀን 2011 ዓ.ም. የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ዓውደ ጥናት እንደሚካሄድ ትላንትና ቫቲካን በሚገኘው የፍትሕ እና የሰላም RealAudioMP3 ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሕንጻ ከተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።
እ.ኤ.አ. 1961 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ ማተር ኤት ማጂስትራ - እናት እና መምህር በሚል ርእስ ሥር፣ የደረሱት ዓዋዲ መልእክት መሠረት ረሩም ኖቫሩም - አዳዲስ ነገሮች በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. በ 1891 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ሊዮነ 13ኛ የወዝአደሩ/የላብአደሩ/ የጉልበት ሠራተኛው ጥያቄዎች ላይ በማነጣጠር ቤተ ክርስትያን ለዚህ ዓቢይ ጥያቄ የምትሰጠው መመሪያ እና ትምህርት የሚያብራራ የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ላይ ተደግፎ የማኅበራዊ ጥያቄዎች ላይ ያተኮረ ቤተ ክርስትያን የምትሰጥበት መልስ አዘል ዓዋዲ መልእክት መሠረት በማድረግ ከባለፈው ዘመን ጀምሮ እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ካሪታስ ኢን ቨሪታተ - ፍቅር በሐቅ የተሰኘው የሰው ልጅ የተሟላ እና የተወሃደ እድገት ላይ ያተኮረ የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ያጠቃለለ መላ የቤተ ክርስያን የማኅበራዊ ትምህርት ሂደት የሚዳስስ ዓውደ ጥናት መሆኑ ሲገለጥ፣ ጳጳሳዊ የፍትሕ እና የሰላም ምክር ቤት ያዘጋጀው ዓዋደ ጥናት በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ 23ኛ እ.ኤ.አ. በ 1961 ዓ.ም. እናት እና መምህር የበሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት 50ኛው ዓመት ለማክበር ብቻ ሳይሆን፣ የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጥያቄዎች መልስ ላይ በማተኮር ከባለፈው ዘመን ጀምሮ ሂደቱ እና እድገቱ በመዳሰስ በወቅቱ በተለይ ደግሞ በዚህ ዓለማዊ ትሥሥር በተረጋገጠበት ዘመን ለሚቀርቡት የማኅበራዊ ነክ ጥያቄዎች የቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት የሚሰጠው መልስ ላይ ጠንቅቆ ለመገንዘብ የሚወያይ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ማሪዮ ቶሶ የፍትሕ እና የሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ስለ ዓውደ ጥናቱ በማስመልከት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ባሰሙት ንግግር በመግለጥ፣ የተወሳሰበውን የወቅቱ የማኅበራዊ ጥያቄ ተጋፍጦ ቀርቦ በጥልቀት መርምሮ ሊያስከትለው የሚችለው ችግር እና ቀውስ ለመከላከል በመሻት እና አደገኛው ሰበቡንም ጭምር ከወዲሁ ለመግታት የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳት ትምህርት መሠረት በተለይ ደግሞ ዓለማዊው ምእመን በሚገባ በዚህ የቤተ ክርስያን የማኅበራዊ ትምህርት ጉዳይ ታንጾ በተሰማራበት የሙያ ዘርፍ እና ኃላፊነት በሥነ ምግባር እና በመንፈሳዊነት ጭምር ተክኖ የቤተ ክርስትያን እናት እና መምህር አቋም እና አመለካከት ለይቶ እንዲገነዘብ የሚያግዝ ዓውደ ጥናት ነው ብለዋል።
ቤተ ክርስትያን እናት እና መምርህ የተሰየመው የር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ ዓዋዲ መልእክት የዓለማዊ ምእመን በሚደራጅባቸው በተለያዩ ማኅበሮች እንቅስቃሴዎች አማካኝነት በማኅበራዊ ጉዳይ ላይ ተቀዳሚ ተወናያን መሆኑ ለይቶ በመገንዘብ፣ ይህ የኅብረሰብ ክፍል የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት በጥልቀት በመመልከት ውሳኔ በመውሰድ በጨረሻም እግብር ላይ እንዲያወለው በነዚህ ሶስት ደረጃዎች የሚከተለው መንገድ በትክልል የሚያሳይ ነው። ስለዚህ የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት በጥልቅ ማጥናት ብቻ ሳይሆን ሠራተኛው ሕዝብ በተሰማራበት ዘርፍ በሥነ ምግባራዊ ኃይል ተነቃቅቶ ሰብአዊነቱን እና እቅዱንም ጭምር በማጣመር የቤተ ክርስትያን ማኅበራዊ ትምህርት በመንግሥት እና በግል ተቋሞች በሰዎች እና በአገሮች መካከል እንዲሁም በመላው አንድ ቤተሰብ በሆነው የዓለም ሕዝብ መካከል እንዲሰርጽ በማድረግ እግብር ላይ ማዋል አስፈላጊ መሆኑ የሚያሳስብ ዓውደ ጥናት ነው ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም በዚህ ዓውደ ጥናት ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ በቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት ሊቃውን በዚህ የቤተ ክርስትያን ተልእኮ አገልግሎት የሚሰጡ ካህናት ዓለማውያን ምእመናን ገዳማውያን የሚገኙባቸው በጠቅላላ 200 ተጋባእያን እንደሚሳተፉም የፍትህ እና የሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፒተር ክድዎ አፒያ ቱርክሱን በመግለጥ፣ ማኅበራዊ ሕይወት በወንጌል እንዲሰበክ የሚያግዝ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለማኅበራዊ ጉዳይ ያቀና የሰው ልጅ አካባቢውን ሕግ እና ፍትሕ እንዲሁም ፖለቲካ ሰብአዊነት ለበስ ለማድረግ ምን መደረግ እንዳለበት የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት መሠረት በማድረግ ሊከተለው የሚገባው መንገድ የሚያመለክት ዓውደ ጥናት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.