2011-05-13 14:42:28

ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ


እ.ኤ.አ. ግንቦት 13 ቀን 1981 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ላይ የተፈጸመው የግድያ ሙከራ ዛሬ 30ኛው ዓመት የሚዘከርበት ዕለት ሲሆን፣ ከሳላሳ ዓመት በኋላ አሁንም በር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ላይ ተጥሎ የነበረው የግድያ ሙከራ በጥልቀት የሚመረምር ስለ ጉዳዩ የሚያትት እና ተጠያቂው የግድያው ሙከራ ዓላማው እቅዱን የወጠነው በጠቅላላ RealAudioMP3 እነዚህ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ማእከል ያደረገ የሥነ ቫትካን ሊቅ ላ ረፑብሊካ ለተሰኘው የኢጣሊያ እለታዊ ጋዜጣ ዘጋቢ ማርኮ አንሳልዶ እና ሳባህ በመባል ለሚጠራው የቱርክ እለታዊ ጋዜጣ በኢጣሊያ ልኡክ ጋዜጠኛ ያሰሚን ታስኪን በጋራ “ር.ሊ.ጳ.ን ግደሉ፣ በዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ላይ የተጣለው የግድያ ሙከራ ዋና ዓላማው” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት መጽሓፍ ለንባብ መብቃቱ ሲገለጥ፣ ስለ ተፈጸመው የግድያ ሙከራ ዓላማው እና ሐቁ ምን መሆኑ ለመለየት የሞከረ መጽሓፍ እንደሆነም የዚህ መጽሓፍ ደራሲ ማርኮ አንሳልዶ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በመጥቀስ፣ ይኸ መጽሐፍ የ20 ዓመት የጥልቅ ጥናት እና ክትትል በተለይ ደግሞ የግድያዊ ወንጀል አጣሪ ፍርድ ቤት እና የመርማሪ ፖሊስ ጽ/ቤት መረጃዎች በማጥናት የግድያው ሙከራ የጣለው አሊ አግካ የቱርክ ተወላጅ በመሆኑም ጋዜጠኛ ያሰሚን በቀላሉ ጉዳዩ በቅርብ ለመከታተል እና አሊ አግካን በወህኒ ቤት እንዲጎበኘው ፈቃድ በማግኘት ስለ ጉዳይ በቀጥታ ከተጠያቂው ጋር በመወያየት፣ ቀጥሎም አሊ አግካ ከወህኒ ቤት ተለቆ ወደ አገሩ ከተመለሰ በኋላም በመገናኘት ያከናወኑት ቃለ መጠይቅ መሠረት በማድረግ የተጠናቀረ መጽሐፍ ነው ብለዋል።

አሊ አግካ እንደሚለውም እስካሁን ድረስ ስለ ተፈጸመው የግድያ ሙከራ የተሰጠው መላምት ያልተስተካከለ ጥቅም የሌለው ነው በማለት ከሰጠው መግለጫ በመንደርደር የግድያው ሙከራ ጠንሳሽ እ.ኤ.አ. ከ 1979 እስከ 1980 ዓ.ም. በቱርክ የነበረው ወታደራዊው መንግሥት ይከተለው ለነበረው የማስፈራራት ዕቅድ ማስፈጸሚያ በመሆን ያገለግል የነበረው የቱርክ የቀኝ ብሔራዊ አክራርያን ኃይሎች እቅድ ነው በሚለው ሐሳብ ላይ የሚጠቃለለ መጽሐፍ ነው።

ሆኖም የወታደራዊው መንግሥት ከተገለጠበጠ በኋላ የዚህ የቱርክ የቀኝ ፖለቲካ ብሔራዊ አክራርያን ኃይል አባላት ወደ ተለያዩ የኤውሮጳ አገሮች ተልከው የተገለበጠውን የቱርክ ወታደራዊ መንሥት ለመደገፍ ያለሙ የተለያዩ የግድያ እና የፍዳታ ሙከራዎች ይጥሉ እንደነበር እና በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ላይ የተፈጸመው የግድያ ሙከራ በዚህ እላይ በተጠቀሰው ዓላማ የሚጠቃለል ነው ብለዋል።

ይኸ የተፈጸመው የግድያ ሙከራ የተከታተለው የሮማ የወንጀል አጣሪ የበላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ኢላሪዮ ማርተላ ስለ ጉዳዩ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ጥይት በመተኮስ የግድያ ሙከራ የፈጸመው አሊ አግካ ብቻ አልነበረም፣ ሆኖም ግን በሕግ እስካሁን ድረስ የዚህ የግድያ ሙከራ ተጠያቂ ሆኖ የተገኘው እርሱ ብቻ ነው። ሆኖም ግን የግድያዊ ሙከራ ፈጻሚ ብቸኛ ተጠያቂ እርሱ ብቻ አይደለም ምክንያቱም ር.ሊ.ጳ. ለመግደል የተተኮሱት ጥይቶች ሶስት ናቸው። ከአግካ የእጅ ሽጉጥ ሁለት ጥይት ነው የተተኮሶው፣ ሶስተኛው ጥይት ታዲያ ከማን ተተኮሰ የሚለው ጥያቄ አስካሁን መልስ አላገኘም። ሌላ በግድያው ሙከራ የተሳተፈ ተጠያቂ እንዳለ ነው የሚያመለክተው። ይኽንን ሐሳብ የሚያብራራ ግንቦት 13 ቀን 1980 ዓ.ም. በሚል ርእስ ሥር በር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ላይ የተፈጸመው የግድያ ሙከራ ማእከል ያደረገ በደረሱት መጽሐፍ ሰፊ ማብራሪያ እንደሰጡበት ገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.