2011-05-11 14:14:32

የስደተኞች እና የተጓዦች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት


ከትላትና በስትያ የስደተኞች እና የተጓዦች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ በአውስትራሊያ ርእሰ ከተማ ሲድነይ በሚገኘው በቅድስት ድንግል ማሪያም ካቴድራል ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በአውስትራሊያ ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ማጠናቀቃቸው ሲገለጥ፣ ቅዳሴውን ሲያቀርቡ ባሰሙት ስብከት፣ ሁሉም አገሮች ጥገኝነት ለሚጠይቁት የፖለቲካ ስደተኞች ተፈናቃዮች በተለያየ ምክንያት ለሚሰደደው በራቸውን እንዲከፍቱ አደራ በማለት፣ ቤተ ክርስትያን በተለያዩ ባህሎች መካከል RealAudioMP3 ግኑኝነት እና ጥልቅ ውይይት እንዲኖር ብቻ ሳይሆን በመቻቻል በሚኖሩት የተለያዩ ባህሎች መካከል ጭምር ውይይት እንዲኖር እንደምታነቃቃ ስለ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ተጓዦች ጉዳይ በተመለከተ የቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት የሚሰጠው ማብራሪያ እና መመሪያ መሠረት በማድረግ ካብራሩ በኋላ፣ አውስትራሊያ ባህላዊ እና ጎሳዊ ኅብረአዊነት የተረጋገጠባት አገር መሆንዋ በማስታወስ፣ ሆኖም ግን ግድ የለሽነት ስለ ሌላው ግድ አለማለት እኔነት ማእከል ያደረገ ከእኔ ወዲያ ማንም የሚል ስስታም ልቅ ራስ ወዳድነት እና ተዛማጅ ባህል ኅብረአዊነትን ለአደጋ ከማጋለጥ አልፎ ሌላው ለመቀበል እና ለማስተናገድ የሚያዘው እና የሚያነቃቃው ስብአዊ ግፊት እንዲዘነጋ እና እንዳይከበር እያደረገ ነው ብለዋል።

ሌላው ሰው ስውር ወይንም የማይጨበጥ ሳይሆን አካል ለበስ በእግዚአብሔር አርአያ እና አምሳያ የተፈጠረ ተምሳያችን ነው። ስለዚህ ይኽ የመሆናችን የላቀው አንድ የሚያደርገን ትርጉም በመዘንጋት ከሌላው ጋር ለመገናኘት የሚያነቃቃው የሚገፋፋው እርሱም ከሌላው ጋር እንድንገናኝ የሚያደርገው በእያንዳንዱ ሰው ዘንድ ያለው ፍላጎት እና ውስጣዊ ነጻነት በተለያየ መልኩ ሲጣስ ይታያል፣ በእያንዳንዱ ሰው ልጅ መካከል ያለው ግኑኝነት በመግባባት በመከባበር ላይ የጸና የሰው ልጅ የተሟላ እድገት የሚያነቃቃ ሆኖ እያንዳንዱ ሰው የተገናኝ ባህርዩ መሠረት ተገቢ ሥፍራው አግኝቶ እንዲኖር ያደርገዋል።

እነሆ በድጅ ቆሜ አኳኳለሁኝ የሚለው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ብፁዕ አቡነ ቨሊዮ በመጥቀስ፣ በር የግል እና የማህበራዊ ጉዳይ የሚለይ የግል እና የማህበራዊ ሕይወት ድንበር መግልጫ ነው። ሆኖም ግን ይኽ በር ድንበር እንጂ የተዘጋ ፈጽሞ የማይከፈት አጥር ማለት አይደለም። ስለዚህ ግለኝነት ልቁ ለእኔ ባይነት ስለ ሌላው ግድ አለ ማለትን እና አለ ማሰብን የሚያነቃቃው ባህል ይህ በር ዘወትር ዝግ ሆኖ ለሚያንኳኳ የማይከፈት እያደረገው ነው። ዛሬ በተለያየ ምክንያት የተለያዩ አገሮች በሮችን የሚያንኳኳ ዜጎች ብዙ ናቸው። ስለዚህ ሌላው ለመቀበል ያለህን ተካፍለህ ለመኖር የሚደግፍ መቀራረብ እና መተሳሰብ የተሰኙትን እሴቶች የሚያነቃቃ ባህል በሁሉም መስክ መስፋፋት አለበት እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.