2011-05-11 13:14:07

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ (11.05.11)


መዝ.63፡1~3 አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ። ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ። ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል። እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፥ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ።

ዉድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፡ ስለ ክርስትያን ጸሎት በምናደርገው ትምህርተ ክርስትያን ጸሎት የሰው ልጅ የጋራ ልምድ መሆኑን ኣይተናል። ዓለማዊነት ወይም ሰኩላሪዝምና ኣውቃለሁ ባይነት በተቆጣጠረውና እግዚአብሔርን በመጋረድ ላይ በሚገኘው ዘመናችን ቁሳዊ የሕይወት ኣመለካከት የዚህ ዓለም ኣስተሳሰብ በቂ እንዳልሆነ በመረዳት ትንሽ የታደሰ የእምነት ስሜት ምልክቶች እየታዩ ናቸው። የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ኣምሳል ተፈጠረ፡ የእግዚአብሔር ፍላጎት በእያንዳንዱ የሰው ልጅ ልብ ኣለ፤ በከፊልም ቢሆን የሰው ልጅ በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መናገር እንደሚችል ያውቃል። ቅ.ቶማስ ዘኣኩኖ ‘ጸሎት እግዚአብሔርን እንደምንፈልግ የሚገልጥ ተግባር ነው፤ ይህ ፍላጎት ራሱ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው፤ ጸሎት ከሁሉም በላይ የልብ ጉዳይ ነው፤ በልባችን የእግዚአብሔርን ጥሪ እንሰማለን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከውስነንታችንና ከኃጢኣታችን ባሻገር ለመጓዝ በእግዚአብሔር እርዳታ እንደምንጠጋ እናውቃለን፤ ጸሎት ስናሳርግ የምንንበረከከው ይህንን ፍላጎት እንዲሁም እግዚአብሔር ለሚሰጠን የምሥጢራዊ የጓደኝነት ግኑኝነት ሥጦታ ክፍት መሆናችንን ይገልጣል’ ይላል።

በጥሞና በልባችን የእግዚአብሔር ድምጽ ለመስማት እንድችልና በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተገለጠልን ዘለዓለማዊ ፍቅሩ ጋር ያለንን ኣንድነት እንድናዳብር ጸሎት እናዘውተር።








All the contents on this site are copyrighted ©.