2011-05-11 14:16:50

ዓለም አቀፍ የመንፈሳዊ መዝሙር ቀን


ዘንድሮ እ.ኤ.አ. ግንቦት ወር መግቢያ ሳምንት በፖላንድ ከ 14 አገሮች የተወጣጡ 700 የሚዚቃ ሥነ ጠበብት የተሳተፉበት የተካሄደው 21ኛው ዓለም አቀፍ የመንፍሳዊ መዝሙር ቀን ለር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ክብር RealAudioMP3 ታስቦ መካሄዱ ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የዘንድሮ የመንፍሳዊ መዝሙር ትርኢት በፖላንድ የባህል ጉዳይ ሚኒስትር የፖላንድ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ድጋፍ ሥር በቼስቶኮቫ በሚገኘው የሃሴት እናት የባህል ማእከል እንዳዘጋጀው ዜኒት የዜና አገልግሎት በመጥቀስ፣ ይህ መንፍሳዊ የባህል ትርኢት መንፈሳዊ መዝሙሮች የቀረበበት መድረክ ብቻ ሳይሆን በሙዚቃ በጠቅላላ በሥነ ጥበብ የሚገለጠው መለኮታዊነት ላይ ያተኮረ ዓውደ ጥናት መካሄዱም የዜናው አገልግሎት በማስታወስ፣ ይህ የመንፈሳዊ መዝሙር ቀን እ.ኤ.አ. ከ 1991 ዓ.ም. ጀምሮ በየዓመቱ የሚካሂድ ሲሆን፣ በዚህ በፖላንድ በተካሄደው የመንፈሳዊ ሙዚቃ ትርኢት ከኦስትሪያ ከጀርመን ከጆርጃ ከስዊድን ከኢጣሊያ ከታላቅዋ ብሪጣኒያ በጠቅላላ ከ14 አገሮች የተወጣጡ ሚዚቀኞች መሳተፋቸው የዜናው አገልግሎት አክሎ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.