2011-05-11 14:40:27

ብፁዕ አቡነ ፎርተ፦ አዲሱ የቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. የረቡዓዊ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ጠቅላይ መሪ ሐሳብ “ጸሎት የሕይወት እስትንፋስ ነው”


በኢጣሊያ የኪየቲ ቫስቶ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ብሩኖ ፎርተ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከባለፈው ረቡዕ ጸሎት የሕይወት እስትንፋስ መሆኑ በማብራራት መደበኛው ተከታታይ ፍጻሜው ጸሎት ላይ ያተኮረ የጀመሩት አዲስ የዕለተ ሮቡዕ ሳምንታዊ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሲያብራሩ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የህልውና ትርጉም ከእግዚአብሔር ምሥጢርና እግዚአብሔር ለዓለም ካለው እቅድ ጋር በማጣመር ካልተፈልገ ሳይታወቅ በጨለማ የሚቀር የተደናገረ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሆኖ ይቀራል፣ ስለዚህ ጸሎት RealAudioMP3 በቅድስት ሥላሴ ዘንድ ያለው የተስፋ አድማስ እንድናወቅ እና በጉዞአችን አመኔታ እንድናደርግ ሕይወታችን ይኸንን ለመገንዘብ የሚያስችለው የሕይወት መልህቅ ጸሎት መሆኑ የሚያዝገነዝብ ትምህርተ ክርስቶስ ነው። ቅዱስ አባታችን ጸሎት የሕይወት እስትንፋስ መሆኑ ሲብራሩ፣ ጸሎት የሰው ልጅ ነጻ የሚያወጣ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዱካ በመመራት የእግዚአብሔር ፈቃድ ለይቶ ገዛ እራሱ እና ታሪክ በዚህ ፈቃድ ሥር እንዲመራ ለማድረግ የሚያስችለው ብርሃን እና ሰላም እንደሚያቀዳጀው ያመለክታሉ።

የሰው ልጅ በመሆናዊው ጥልቅ ትርጉም መሠረት፣ ብቸኛ ነገር ወይንም ተነጥሎ የሚኖር ኅልውናው በገዛ እራሱ ላይ የጸና ወይንም ገዛ እራሱ ማለት አይደለም፣ ስለዚህ በእግዚአብሔር የፍቅር ቃል ኪዳን የተፈጠረ የእግዚአብሔር ተባባሪ፣ እግዚአብሔር ፈቅዶት በነጻ ከእርሱ ጋር የሚወያይይ የሚነጋገር ጠቅለል ባለ አገላለጥ፣ ሰው የእግዚአብሔር ገጽ ለማስተንተን በእግዚአብሔር የተፈጠረ መሆኑ የሚያስተምር ነው። ቅዱስ አጎስጢኖስ በኑዛዜ መንፈሳዊ ድርሰቱ እንደሚያመለክተው እግዚአብሔር ሆይ ልባችን ላንተ ነው የፈጠርከው በአንተ እስካላረፈ ድረስ ግን የተረበሸ ሆኖ ይቀራል በማለት የሰው ልጅ ለምን እንደተፈጠረ በጥልቅ ይገልጥልናል፣ ስለዚህ የሰው ልጅ በእውነተኛ እና በጥልቅ መንፈስ ሲጸልይ ገዛ እራሱን በፈጣሪ ፊት ያቀርባል።

ጸሎት እና መጸለይ ዘወትር መማር ያስፈልጋል፣ የጸሎት ትምህርት ቤት እጅግ አስፈላጊ ነው። ምክንያቱ ጸሎት ቀመር አይደለም፣ የሰው ልጅ ገዛ እርሱን በጥልቀት ለዘለዓለማዊው የሕይወት ምንጭ ለሆነው እግዚአብሔር ክፍት አድርጎ ለማቅረብ መጸለይ መማር አለበት፣ ቅዱስ አባታችን ይኸንን ሁሉ እግምት ውስጥ በማስገባት ጸሎት በእግዚአብሔር ዘንድ እንድንሰምጥ እና ከጥልቅ ሰብአዊነታችን ጋር እንድንገናኝ በእያንዳንዱ ሰውል ልጅ ዘንድ ያለው እውነት መልካም ከሆነው እግዚአብሔር ጋር እንድንገኛ ሰብአዊነታችንን በጥልቀት ያጎናጽፈናል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.