2011-05-11 14:43:59

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ በክርስትያንነቱ የተማመነ ክርስትያናዊ ምስክርነት ታማኝ ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከትላትና በስትያ እና ትላትና እሁድ በኢጣሊያ ሰሜናዊ ምስራቅ ክልል ሐዋርያዊ ጉብኝት ማካሄዳቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስነታቸው ቅዳሜ ከቀትር በኋላ በቨነዚያ የአየር ማረፊያ እንደደረሱ በቨነዚያ ፓትሪያርክ ብፁዕ ካርዲናል አጀሎ ስኮላ በጎሪዚያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲኖ ደ አኖትኒ በኢጣሊያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪልRealAudioMP3 ብፁዕ አቡነ ጁዘፐ በርተሎ እና የአካለ ስንኩላ ሕጻናት እና በተለያየ ችግር ለአደጋ የተጋለጡት ሕጻናት እና ታዳጊ ወጣቶች መርጃ ማእከል አባላት እና የዚህ መርጃ ማእከል ተረጅ አካለ ስንኩላን ሕጻናት በክልሉ የመንግሥት ተወካዮች እና የመስተዳዳር የበላይ አካላት ጭምር አቀባበል ተደርጎላቸው በቀጥታ ወደ አኵለያ አደባባ በመሄድ ለቨነዚያ ከተማ ከንቲባ የምክር ቤት አባላት እና የከተማይቱ ባለ ሥልጣናት ለውሉደ ክህነት አባላት እና በጠቅላላ ለሁሉም ምእመናን ሰላምታን ካቀረቡ በኋላ የትሪቨነቶ ሰበካ ተጠሪዎች ጋር መገናኘታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ቅዱስ አባታችን በአኵለያ አደባባይ ባሰሙት ንግግር፣ በዚህ በምንኖርበት ዘመን እና ታሪክ በክርስትናው ታምኖ የሚያሳምን አስተማማኝ ክርስትያን አስፈላጊ ነው በማለት ካሳሰቡ በኋላ የሰው ልጅ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ተስፋ የሚቀበለው፣ ስለዚህ መጪው ሕይወት ብሩህ ይሆን ዘንድ እና መሠረታዊ ትርጉሙን ጠንቅቆ ለመለየት ይቅር በመባባል ብርታት ፍትህ እና ሰላም የተረጋገጠለት ለማድረግ የሚቻለው ክርስቶስ በሚሰጠው ኃይል ብቻ ነው። ማኅበረ ክርስትያን ይኸንን መሠረታዊ መንፈሳዊነት በጽናት እና በመቆ ልብ በመኖር ይኸንን ለመመሥከር ብርታት የሚሰጠውን የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውን እና ደሙን በመመገብ እንዲኖር አደራ ካሉ በኋላ፣ በመጨረሻም የአኵለያ እመ ቤተ ክርስትያን ቅድስት ድንግል ማርያም የክልሉ ማኅበረ ክርስትያን እምነቱን በውህደት እና በመደጋገፍ ብሎም በኵላዊነት መንፈስ እንዲኖረ ትደግፍ ዘንድ በመማጠን ንግግራቸው እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ቅዱስ አባታችን የኢጣሊያ የስሎቨኒያ የክሮአዚያ አውስትሪያ እና ጀርመን በጠቅላላ ከ36 ሰበካዎች የተወጣጡ በተለይ ደግሞ በትሪቨነቶ እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. ሊካሄድ ተወስኖ ያለው የቤተ ክርስትያን ጉባኤ የተዋጣለት ይሆን ዘንድ ከወዲሁ እያከናወነቱ ያለው ቅድመ ዝግጅት በማድነቅ፣ በዚህ በታሪክም ሆነ በማህበራዊ ሕይወት ደረጃ በመታየት ላይ ያለው ለውጥ ክርስትያን በክርስትናው የተማመነ ለማሳመን የሚችል እንዲሆን የሚጠይቅ ክስተት ነው። ስለዚህ ማንኛውም ስለ እምነታችንን ለሚጠይቀን በችግር በዋስትና እጦት በመጠቃት ለመንኮታኮት አደጋ የተጋለጠው ሁሉ የምናምነው የእምነታችን ተስፋ በጠቅላላ ለምን ማመናችን የተሟላ በ ሥነ አመክንዮ የተደገፈ መሠረታዊ ምክንያት ለማቅረብ የምንችል መሆን ይጠበቅብናል።

ለሌሎችን የምናሳምን ሆነን እንድንገኝ የምናምነው ወንጌል የሚክድ ሕይወት ከመኖር፣ የምናምነው ወንጌልን የሚጻረር ሕይወት ከመኖር በመቆጠብ እንዲሁም ክርስትናን የሚያጥላላ እና በክርስትና ላይ የጸናውን መሠርቱን የሚክድ በመስፋፋት ላይ ያለው ሰብአዊነት ከወንጌል ጋር የተቀናጀ እና የተሳካ ሕይወት በመኖር ከተማችሁ ሰብአዊነት ልክ ያላት ቅን እና አስተናጋጅ በማድረግ አሳማኝ ክርስትያኖች ሆነን መገኘት ይገባናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.