2011-05-11 14:15:40

ለሚወለደው ሕጻን አሳቢነት አማካኝነት ቤተሰብ መመልከት


የአንድ ቤተሰብ ሚዛን ለሚወለደው ሕፃን አሳቢነት መሆን እንዳለበት የቤተሰብ ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኤኒዮ አንቶኔሊ ስለ ቤተሰብ ጉዳይ የሚንከባከበው የግብረ ሰናይ ማኅበር በኢጣሊያ ሳሌርኖ ከተማ ቤተሰብ እና ሕፃናት በሚል ርእስ ሥር ተሸኞት ላካሄደው ጉባኤ ባስተላለፉት መልእክት በማስታወስ፣ ብዙውን ጊዜ ስለ ቤተሰብ በተመለከተ በሚደረጉት RealAudioMP3 ውይይቶች እና የተለያዩ መንግሥታት ጭምር የሚከተሉት የቤተሰብ ጉዳይ ፖለቲካ ከቤተሰብ ኃላፊዎች በመንደርደር እንጂ የቤተሰብ አባላት የሆኑትን ሕፃናት ማእከል ከማድረግ የሚመነጭ እንዳልሆነ ብፁዕ ካርዲናል አንቶነሊ በመግለጥ፣ ስለዚህ ቤተሰብ ለሕፃናት አሳቢነት ከሚለው ውሳኔ በመንደርደር ከሕፃናት ጎን ሆኖ ቤተሰብን የሚንከባከብ እቅድ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።

የእያንዳንዱ ሕፃን የተሟላ እድገት እንዲረጋገጥ የሚደግፍ ሕፃናት ወይንም የሚወለደው ሕፃን ማእከል ያደረገ የቤተሰብ ደጋፊ እቅድ እጅግ አስፈላጊ ነው። ወላጆች ለተቀበሉት የኃላፊነት ጥሪ ታማኞች በመሆን የልጆቻቸውን የተሟላ እድገት ዋስትና መስጠት እንዲችሉ፣ የመንግሥታት ድጋፍ እንደሚያሻቸውም ብፁዕነታቸው በማብራራት፣ ቤተሰብ የሚሰዋው የጌታችን ኢየሱስ ፍቅር የሚረጋገጥበት መተሳሰብ መደጋግፍ የጸናበት ለሚወለደው ሕፃናት የሚያስብ በእነዚህ ሕፃናት ሚዛን የሚለካ መሆን አለበት። ስለዚህ ስለ ሕጻናት ግድ የሚል ቤተሰብ እና ለሕፃናት አባላት የሚያስብ ቤተሰብ የተረጋገጠበት ማኅበረሰብ መተሳሰብ እና መደጋገፍ የሚረጋገጥበት እንደሚሆን አያጠራጥርም እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.