2011-05-09 15:31:57

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ ገዛ እርሳህን ወደ ላይ በሚያቀና ሕይወት መምራት


በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜና እና ኅትመት ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አሰዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ መሠረት፣ ዱክ ኢን አልቱም፣ ወደ ላቀው መንፈሳዊው ጉዳይ በማቅናት ገዛ እራስህ ምራ በሚል ርእስ ሥር፣ ይኸው ኵላዊት ቤተ ርክስትያን ለር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ብፅዕና ያወጀችበት ሳምንት መሆኑ በማስታወስ፣ እኚህ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በመሆን ቤተ ክርስትያንን ለረዥም ዓመታት እምነትን በማጽናት የመሩ አባት፣ ቤተ ክርስትያን ብፅዕና ባወጀችላቸውት RealAudioMP3 ዕለት የታየው የሕዝብ ተሳትፎ የመንግሥታት መሪዎች በፅዕና በታወጀበት ዕለት የተገኙት ሁሉ እና የተፈጸመው መንፈሳዊ ንግደት በጠቅላላ በሚያስደንቅ ኅብረአዊነት የታየው ሱታፌ የመሰከረው መሆኑ በማስታወስ፣ የር.ሊ.ጳ. ብፅዕ ዮሓንስ ጵውሎስ ዳግማዊ የግል ዋና ጸሓፊ በመሆን ያገለገሉት በአሁኑ ወቅት የክራኮቪያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ስታኒስላዊ ድዝዊች በእውነት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በመካከላችን ናቸው በማለት ለበዓለ ብፅዕና ዋዜማ በሰጡት ምስክርነት ያሉትን ሐሳብ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ በመጥቀስ የር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ብፅዕና እግዚአብሔር ለቤተ ክርስትያን እና ለምእመናን የሰጠው ጸጋ ነው ብለዋል።

አባ ሎምባርዲ ርዕሰ አንቀጹን በመቀጥል የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እና ወጣቶች መካከል የነበረው ግኑኝነት ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል በብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የነረው ሥፍራ ጋር በማያያዝ አስታውሰው፣ ቤተ ክርስትያን ለዚህ የኅብረትሰብ ክፍል አቢይ ትኵረት እንድትሰጥ በአዲስ መንፈስ ያነቃቃ እና የመራ አገልግሎት መሆኑ በማብራራት፣ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሕዝብ ወደ ላቀው ክብር እንዲያተኩር በማሳሰብ ቤተ ክርስትያንን ወደ ሶስተኛው ሺሕ ዓመት ያሸጋገሩ እና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታዮ እንዲሆኑ ተሹመው አትፍሩ ልባችሁ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክፈቱለት በማለት ባቀረቡት ጥሪ መሠረት ካስጀመሩት ቤተ ክርስትያናዊ ጉዞ ቀጥለው አሁንም ስለ ቤተ ክርስትያን እና ስለ ምእመናን በጠቅላላ ስለ ዓለም ሕዝብ እያማለዱ ናቸው፣ ከሰማይ ቤት ሆነው አሁንም ሕዝበ እግዚአብሔርን ቤተ ክርስትያንን በእምነት እያጸኑ ናቸው፣ ብዙ ጊዜ ቡራኬአቸውን ተቀብለናል ዛሬ እንዲባርከን እንጸልያለን ሲሉ ርእሰ አንቀጹን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.