2011-05-09 15:29:40

የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ተልእኮ


በኢጣሊያ የኡዲነ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አድረያ ብሩኖ ማዞካቶ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በአኵለያ እና በመቨነዚያ ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የቅዱስ አባታችን ሐዋርያዊ ጉብኝት ወድሞችን በእምነት አጽና በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጴጥሮስ የሰጠው ተልእኮ የሚኖር እና የሚያረጋገጥ ነው። ስለዚህ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ RealAudioMP3 እምነታችን ለማበረታታት እና ለማጽናት የሚፈጽሙት ሐዋርያዊ ጉብኝት መሆኑ መዘንጋት የለብንም።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህች በክርስትናው እምነት ጥንታዊ ክልል ተብለው በሚጠቀሱት ክልሎች የፈጸሙት ሐዋርያዊ ጉብኝት፣ የክልሉ ክርስትያናዊ መሠረት ያለው ሃብታሙን ባህል የሚያነቃቃ የክልሉ ሕዝብ ይኸንን ቅዱስ ታሪክ እንዳይዘነጋው አደራ የሚል እና የሚያስገነዝብም ነው ካሉ በኋላ፣ በዚሁ ክልል በዘመናችን እየተስፋፋ ያለው ተዛማጅ ባህል የሚታይበት በመሆኑም፣ በርግጥ ከዚህ ባህል ለመጠንቀቅ እና በቃል እና በሕይወት እንዲሁም በሥነ አመክንዮ የተደገፈ ምስክርነት ውድቅ እንድናደርገው ለዚህ ጥልቅ የእምነት ጉዞ የሚያናቃቃ ሐዋርያዊ ጉብኝት ነው።

በመጨረሻም በዚህ የበዓለ ትንሣኤ መንፈስ በመኖር ላይ በምንገኝበት ወቅት ይላሉ ብፁዕ አቡነ አንድረያ ብሩኖ ማዞካቶ የቅዱስ አባታችን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለውሉደ ክህነት አባላት በክህነታዊ ጥሪያቸው የታመኑ ምስክሮች እንዲሆኑ የሚጠይቅ ጥሪን የሚያነቃቃ ቤተ ሰብን በክርስትያናዊ ሕይወት የሚደግፍ እያንዳንዱ በጥሪው አማካኝነት ክርስቶስን እንዲከተል እና እንዲመሰክር የሚደግፍ ጸጋ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.