2011-05-09 15:30:58

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለካቶሊክ ተግባር ማኅበር መልእክት አስተላለፉ


14ኛው ጠቅላይ ጉባኤ በማካሄድ ላይ ለሚገኘው ለኢጣሊያው ብሔራዊ የካቶሊክ ተግባር ማኅበር ቅዱስ አባታችን ዓለማዊ ምእመን አስተማማኝ በእምነት የታመነ እንዲሆን ጥሪ በማቅረብ ኤውሮጳ የዘመኑ ሁለ ገባዊ ተጋርጦ ለመቅረፍ እንድትችል እና ተገቢ መልስ ለመስጠት ትችልም ዘንድ ክርስትያን ምእመን በመተባበር እና በመደጋገፍ ከሚሰጠው አገልግሎት ባሻገር የእምነት ውበት እና መሠረታዊ RealAudioMP3 ምክንያት ወይንም ልቦና ለመመሥከር የተጠሩ ናቸው ብለዋል።

በብሔራዊ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የካቶሊክ ተግባር ማኅበር ከውሉደ ክህነት አባላት ጋር እና በተለይ ደግሞ ከመንበረ ጴጥሮስ ውህደት ካላቸው ብፁዓን ጳጳሳት እና ብፁዓን አቡኖች ጋር በመተባበር እና በእነርሱ በመመራት የሚሰጠው አገልግሎት ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት በመጥቀስ አመስግነው፣ ይህ ማህበር ባለው እየተለዋወጠ በሚሂደው በዘመናችን የባህል ታሪክ የሕንጸት ማኅበር መሆኑ ከቤተ ክርስትያን ጋር ባለው ኅብረት እና በቤተ ክርስትያን መሪነት ሥር የሚሰጠው አገልግሎት የመሰከረ፣ ወጣት የኅብረተሰብ ክፍል በማነጽ የሚሰጠው አስተዋጽዖ ጭምርም በመጥቀስ፣ አክለው ከተለያዩ የቤተ ክርስትያን እና የመንግሥት የሕንጸት መዋቅሮች ጋር በመተባበር የሚሰጠው የተሟላ የሕንጸት አገልግሎት እንዲቀጥልበት አደራ እንዳሉም የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ሁሉም ለቅድስትና መጠራቱንም በመግለጥ፣ ቅድስትና አበይት ተግባሮች በመፈጸም ተአምር በመሥራት የሚፈጸም ብቻ ሳይሆን፣ በእለታዊ ኑሮ በተጠራንበት ጥሪ አማካኝነት በምንሰጠው አገልግሎት ታማኞች በመሆን በምንሰጠው ዕለታዊ ምስክርነት የሚኖር ጸጋ ጭምር መሆኑ ገልጠው፣ ይኽ ደግሞ ለመንፈስ ቅዱስ ተግባር ዝግጁ ሆኖ መኖር ማለት መሆኑንም አብራርተው፣ ቅድስና ለወንጌል ለቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት ታማኞች በመሆን የሁሉም ጥቅም እንዲረጋገጥ በሚል ዓላማ በማገልገል በእለታዊ ኑሮአቸው የክርስትናው መሠረታዊው መመሪያ ታማኝ ሆኖው መኖር ማለት ነው ብለዋል።

ዓለማዊው ካቶሊክ ምእመን በማኅበራዊ ጉዳይ ማለትም በባህል በፖለቲካው መድረክ የሚሰጠው አገልግሎት በወንጌል የታነጸ መሆን እንዳለበትም በማሳሰብ፣ በኢጣሊያ የተረጋገጠው እድገት እና በመረጋገጥ ላይ ያለው ሁለ ገባዊ አወንታዊ ሂደት የካቶሊክ ምእመናን አስተዋጽዖ መሠረት ያለው መሆኑ የማይካድ ሓቅ ነው በማለት፣ የኢጣሊያ የወቅቱ ማኅበራዊ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊው ሂደት የክርስትያን ምእመናን ባህላዊ ብቃት እና መንፈሳዊነት በሥነ ምግባር እና በግረ ገብ የተካነ አገልግሎት የሚጠይቅ በመሆኑም ከዚህ አኳያ የክርስትያን ምእመን አቢይ ኃላፊነት ምን መሆኑ ለመገመቱ አያዳግትም፣ በጠቅላላ በአንዳንድ የመካከለኛ ምሥራቅ አገሮች እና በሰሜን አፍሪቃ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመጽ ምክንያት ከክልሉ የሚሰደዱ እና የሚፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ በሚደረገው ርብርቦሽ ክርስትያን ምእመን ቀዳሚ ሆኖ ሊገኝ እንደሚገባውም በማሳሰብ፣ በሁሉም ተግባር በክርስቶስ ላይ ያለን እምነት መሠረት ነቅተን በመሳተፍ ይኸንን እምነት በቃል እና በሕይወት መመስከር ይኖርብናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.