2011-05-06 17:03:24

ፕረሲዳንት ኦባማ የቢን ላደን የሬሳ ስእል ይፋ አሆንም ማለታቸው ፡


የዩናይድ ስቴትስ መንግስት መሪ ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ትናትና ኒውዮርክ ላይ የሚገኘው እኤአ መስከረም 11 ቀን 2001 በሽብርተኞች የወደመው Ground Zero አለም አቀፍ የንግድ ማእከል መጐብኘታቸው ከዚሁ ቦታ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ በዚሁ የሽብርተኞች ሰለባ የሆነ ቦታ ጉንጉን አበባ አስቀምጠዋል አደጋ በተቃጣበት ግዜ ከሞት ከተረፉ ሰዎች ጋርም መገናኘትቸው ዜናው ለጥቆ አመልክተውል።

ግራውንድ ዜሮ ዓለም አቀፉ የንግ ማእከል በተጠቃበት ግዜ ከሶስት ሺ በላይ ሰዎች መገደላቸው የማይረሳ ነው።

ማእከሉ እንዲጠቃ ያቀዱ እና ሽብርተኞች ያለኩ የአልቃዒዳ የተባለ ሽብረተኛ ቡድን መሪ እሳማ ቢን ላደን ባለፈው ሰኞ ፓኪስታን ውስጥ አቦታባድ በተባለ ቦታ በየአመሪካ ልዩ እዝ ሰንሰለት መገደላቸው የሚታወስ ነው ።

ይሁን እና ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ሽብረተኛ ቢን ላደን መገደሉ አረጋግጠው የሬሳ ስእል ግን ለአመሪካ ብሔራዊ ጸጥታ አሉታዊ ስለ ሆነ ለዓለም ይፋ እንደማይሆን ከትናንትና ወድያ ለcbs የዜና አውታር መግለጣቸው የሚታወስ ነው።

ይሁን እና የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ረዳት ፕረሲዳንት ጆ ባይደን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮድሃም ሂላሪ ክሊንተን እና የመከላከያ ሚኒስትር ሮብርት ጌትስ ከፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ውሳኔ ጋር እንደሚስማሙ ከዋሺንግቶን የመጣ ዜና አስታውቅቀዋል። ጉዳዩ አነጋገሪ እየሆነ መምጣቱ እየተነገረ ነው።

በተባበሩት መንግስታት የሰው መብት ተካራካሪ ድርጅት ኮሚሽነር ነቪ ፒለይ እንደገለጡት ፡ ዩናይትድ ስቴትስ የቢን ላደን ግድያ በተመለከት ዝርዝር ማብራርያ ትሰጥ ዘንድ መጠየቃቸው ከጀነቭ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆነ ስብረተኛ ኦሳማ ቢን ለዳን ለበርካታ ዓመታት ርእሰ ከተማ ኢስላማባድ አቅራብያ በአንድ ቪላ እየኖሩ የፓኪስታን መንግስት አለወቅኩም አላያሁም አላውቅኩም በማለትዋ ዩናትድ ስቴትስም አባባሉ ባለ መቀበልዋ የተነሳ በሁለቱ ሽብርተኛነት በጋራ እንዋጋለን በሚሉ ሀገራት መካከል አለመጣጣም መከስቱ ተመልክተዋል።

በሌላ በኩል የፓኪስታን መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ዩናይትድ ስቴትስ የፓኪስታን ልዓላውነት በመጣስ በግልዋ የሰደችው ርምጃ ሕጋዊ አይደለም ማለት መጀመራቸው ሌላ ከኢስላማባድ የመታ ዜና ዘግበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.