2011-05-06 15:32:41

የሙዚቃ ኮንሰር ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ክብር


የኢጣሊያ ሬፓብሊክ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ ትላትና በቫቲካን ጳውሎስ ስድስተኛ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዘንድሮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ላከበሩት 7ኛ ዓመት ስምየተ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምክንያት በስፐይን ተወላጅ ኾሰ ሎፐዝ ኮቦስ በተመራ የሮማ የሙዚቃ እና የትያትር ቤት ዘማርያን ኦርኬስትራ RealAudioMP3 የሮሲኒ ሳባት ማተር - ቅድስት ድንግል ማርያም በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት ይላዌ በተለይ ደግሞ በመስቀል ተሰቆሎ በስቃይ ላይ እያለ ማርያም በመስቀሉ ሥር ቆማ ነበር (ማርያም በማዳን እቅድ ሱታፌ የሚያገልጥ)፣ የስቃዩ ተካፋይነቷን የሚያወሳው ታሪክ እና የተአምኖተ ሃይማኖት ውሁድ ጣዕመ ሙዚቃ መቅረቡ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ፣ ነው።

የሚዚቃው ትርኢት እንዳበቃ የኦርኬስትራው መሪ ኼሴ ሎፐዝ ኮባስ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የቀረበው የተወሃደ ጣዕመ ሙዚቃ ለቅዱስ አባታችን ክብር በመሆኑ ይህ ኦርኬስትራ ከተለያዩ መንፈሳዊ ውሁድ ጣዕመ ሙዚቃዎች ውስጥ እንዲመርጡ ጠይቆአቸው ሲያበቃ ይኸው ኦርኬስትራው ምርጫቸውን በማክበር ለክብራቸው ሳባት ማተር እና ተአምኖተ ሃይማኖት የሙዚቃ ድርሰቶች ለማቅረብ በቅተዋል።

ሮሲኒ በዚህ የሳባት ማተር የሙዚቃ ድርሰቱ አማካኝነት በእርግጥ በስቃይ ዘንድ ከስቃው ወዲያ ያለው መጽናናት በጠቅላላ ስቃይ የድህነት ጎዳና መሆኑ በጥልቅ ለማስገንዘብ የቻል በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ ስር የማርያም ስቃይ በማውሳት የስቃይ ትርጉምን የገለጠ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.