2011-05-06 15:53:57

በነዲክቶስ 16ኛ ሰሜናዊ ምስራቅ ጣልያን ይጐበኛሉ ፡


በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ነገ ግንቦ ሰባት ቀን እንደ በጎርጎርዮስ አቁጣጠር በሰሜናዊ ምስራቅ ጠልያን የሁለት ቀናት ሐዋርያዊ ዑደት እንደሚያደርጉ ቫቲካን አስታውቀዋል።

በዚሁ ቫቲካን ያወጣው መርሃ ዑደት ቅድስነቶም መሠረት በነዲክቶስ ነገ ከቀትር በኃላ ከሐውራያዊ መንበራቸው ተነስተው በትሪቨንቶ ሀገረ ስብከት ወደ ሚገኘው አኲለያ ወደ ተባለችው ከተማ ያቀናሉ ።

ከአኲለያ ከተማ ተንስተው ውደ ቨኒስ ከተማ ተጉዘው በቅዱስ ማርቆስ አደባባይ ከከተማይቱ ህዝብ እንደሚገናኙ ሐዋርያዊ መርሃ ዑደቱ አስታውቀዋል።

ከነገ ወድያ ሰንበትም ቨነጺያ ከተማ አቅራብያ ወደ ምትገኘው መስትረ ከተማ ጐራ በማለት እዚያው በከተማይቱ በሚገኘው ትልቅ ሜዳ መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚያሳርጉ ተገልጠዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በስድስት ዓመታት ርእሰ ሊቃነ ጳጳስናቸው ግዜ ጣልያን ውስጥ ሃያ ሁለተኛ ሐዋርያዊ ዑደት እያካሄዱ እንደሚገኙ የቫቲካን መግለጫ አያይዞ አስታውሰዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ የቨነጺያ ከተማ ፓትርያርክ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ የቅድስነታቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት አስመልክተው መግለጫ ሲሰጡ ፡ ቅድስነታቸው የዚሁ የሰሜናዊ ምስራቅ ጣልያን ክልል ካቶሊካዊ እምነታችን ለማረጋገጥ በኛ መካከል ይገኛሉ ።








All the contents on this site are copyrighted ©.