2011-05-06 15:24:40

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ ቅዱስ መጽሓፍ ጠንቅቆ ለመገንዘብ መለኮታዊ አስተንፍሶ ምንጩን አለ መዘንጋት


እዚህ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት መርታ ሕንጻ እ.ኤ.አ. ከግንቦት 2 ቀን እስከ ግንቦት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. የቅዱስ መጽሓፍ ድርገት “የቅዱስ መጽሓፍ አስተንፍሶ እና እውነት” በሚል ርእስ ጉዳይ ተመርቶ ዓመታዊ ጉባኤ ማካሄዱ ሲገለጥ፣ ዓመታዊው ምልአተ ስብሰባውን በሊቀ መንበርነት የመሩት የካቶሊክ አንቀጸ ሃይማኖት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ዊሊያም ጆሴፍ ለቫዳ RealAudioMP3 ሲሆኑ፣ እንዲሁም የጉባኤው ውይይት የመሩት የዚህ ድርገት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ክለመንስ ስቶክ መሆናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መጽሓፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር መለኮታዊ አስተንፍሶ የመነጨ መሆኑ ከተዘነጋ ለመረዳቱም ሆነ ጠንቅቆ ለመገንዘብ ፈጽሞ የሚያዳግት ይሆናል፣ የሚል ሐሳብ ማእከል ያደረገ ለጉባኤው ያስተላለፉት መልእክት በብፁዕ ካርዲናል ዊሊያም ለቫዳ በኩል ለጉባኤው መነበቡ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት መጽሐፍ ቅዱስ በርግጥ መለኮታዊ ክስተት ያነቃቃው ነው የሚለው ኅልዮ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል በሰው ልጅ ቃል የተጻፈ መሆኑ ለመረዳት የሚግዝ መሠረታዊ ግንዛቤ ነው ለሚለው እውነት መሠረት ወሳኝ መሆኑ ቨርቡም ዶሚኒ - ቃለ እግዚአብሔር በሚል ርእስ ሥር ባስተላለፉት ሐዋርያዊ ምዕዳን ያሰመሩበት ነጥብ በመጥቀስ፣ ስለዚህ ቅዱስ መጽሐፍ መለኮታዊ ክስተቱን እና መለኮታዊ አስተንፍሶ ያነቃቃው ነው የሚለው ሥርወ ነገሩ (ኣናሥር) እግዚአብሔርብሔ መሆኑ የሚያረጋግጠው እውነት መዘንጋት የቅዱስ መጽሐፍ አስፈላጊነቱ እና እጹብ ድንቅ የሚያሰኘው ባህርዩን ግምት አለ መስጠት ማለት ይሆናል። ይኸንን እግዚአብሔራዊ ሥወ ነገሩ ግምት አለ መስጠት፣ ቅዱስ መጽሐፍ ዝቅ አድርጎ በሚመለከት አይነት አገላለጥ የሚተነተን ብቻ ሆኖ ይቀራል። ለእኛ ያለው ሊገመት የማይቻለው የላቀው ክብሩንም ያጣል። ስለዚህ እንዲህ ባለ መልኩ የቅዱስ መጽሐፍ ወደር የሌለው ክብሩን ግምት የማይሰጥ አይነት ሥነ ትንተና ቅዱስ መጽሐፍ የሰው ልጅ ቃል የወለደው የላቀ እና የጥልቅ ውበት መግለጫ ስለዚሆ የፈጠራ ሥራ ውጤት ሆኖ ይቀራል።

እግዚአብሔር በቃሉ ከእኛ ጋር ይወያየል በቃሉ ወደ እኛ ይመጣል፣ የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔር ማንነት እና የፈቃዱ ምሥጢር መግለጫ ከመሆኑ ባሻገር የማዳን እቅድ ማረጋገጫም ነው። ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ማወቅ እና ማግኘት እግዚአብሔርን በበለጠ ማወቅ እና ከእግዚአብሔር ጋር መተዋወቅ ብሎም አዳኝ የሆነው የፈቃዱን እቅድ ምሥጢር ማወቅ ማለት መሆኑ ቅዱስነታቸው አብራርተዋል።

ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚደረገው ቲዮሎጊያዊ አስተንትኖ / ትንተና፣ ዘወትር መጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊ አስተንፍሶ ያነቃቃው (የመለኮታዊ አስተንፍሶ ክስተት) እና እውነት መሆኑ እንደማይዘነጋው ቅዱስ አባታችን ባስትላለፉት መልእክት በማስታወስ፣ ይህ ደግሞ የቅዱስ መጽሐፍ ቤተ ክርስትያናዊ ሥነ ትንተና የሚከተለው መሠረታዊ ኅልዮ ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ለመገንዘብ እና ለመተንተን ቤተ ክርስትያናዊ ሥነ ሥልት፣ ቅዱስ መጽሐፍ መለኮታዊ አስተንፍሶ እና እውነት ነው የሚለው ኅልዮ መሠረት ያደረገ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። በእያንዳንዱ የቅዱስ መጽሐፍ ዘንድ የተጠቃለሉት ቅዱሳት መጻሕፍት እራሱ የቻሉ ነገር ግን ወደ ሙላት ያተኮረ የእግዚአብሔር ታሪክ ውህደት መግለጫ ይሆናሉ ካሉ በኋላ፣ በመጨረሻ ይህ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 20 ቀን 1902 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ሊዮነ 13ኛ ውሳኔ የተቋቋመው ጳጳሳዊ የቅዱስ መጽሐፍ ድርገት ቅዱስ መጽሐፍ በጥልቅ ለማወቅ እና ለማጥናት ብሎም በትክክል በመረዳት በሕይወት ለመቀበል እንዲቻል በሚደረገው ጥረት የሚሰጠው አገልግሎት በማድነቅ ምስጋና ማቅረባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.